1 / 8

፫ . የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ

፫ .1 የሕመም እና የብግነት አያያዝ. ሞርፊን

Download Presentation

፫ . የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ

An Image/Link below is provided (as is) to download presentation Download Policy: Content on the Website is provided to you AS IS for your information and personal use and may not be sold / licensed / shared on other websites without getting consent from its author. Content is provided to you AS IS for your information and personal use only. Download presentation by click this link. While downloading, if for some reason you are not able to download a presentation, the publisher may have deleted the file from their server. During download, if you can't get a presentation, the file might be deleted by the publisher.

E N D

Presentation Transcript


  1. ፫.1 የሕመም እና የብግነት አያያዝ ሞርፊን ከ1800ዎች መባቻ ጅምሮ የሕመምን ስሜት ለመቀነስ ጥቅም ላይ የዋለው ሞርፊን የሚቀመመው ከጥሬ ኦፒየም ነበር፡፡ ሁንጋሪያዊው ፋርማሲስት ያኖሽ ካባይ በ1920ዎች ውስጥ ሞርፊንን ከጥሬ የፖፒ አበባ ብቻ ሳይሆን ከደረቅ የፖፒ ገለባ ጭምር በማምረት ስር-ነቀል ለውጥ አመጣ፡፡ የእጹ ኬሚካዊ መዋቅር ሱስ አስያዥነትን እና የእስትንፋስ አካላት መታወክን ከመሳሰሉ የማይፈለጉ ንብረቶች ነጻ ሆኖ ሕመም-አሰታጋሽነቱን ለማረጋገጥ በ1923 ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡ ተፈጥሯዊው ቅመማ እንዴት በሰው አካል ውስጥ እንደሚሠራ ማወቅ በ1961ናሎርፊንን እና ናሎክሶንን የመሳሰሉ ረጋ-ሠራሽ የሞርፊን ዝርያዎች እንዲቀመሙ እና አስተማማኝ እንክብሎች እንዲፈጠሩ መንገድ ጠረገ፡፡ ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ቡዳፔሽት፣ ሁንጋሪያ ውስጥ የያኖሽ ካባይ የመቃብር ሐውልት አሰፒሪን ሳሊክሊክ አሲድ የማይፈለጉ የጎን-ውጤቶች (ማቅለሽለሽ፣ የጨጓራ መምገል፣ ወዘተ.) የሚያስከትል ቢሆንም እንኳ፣ በ1890 ውስጥ ለደም-ስር ሪህ (rheumatoid arthritis) ብግነት ፈዋሽነት እንደ እርካሽ እና ውጤታማ መድሐኒት ይመረት ነበር፡፡ አሴቲልሳሊክሊክ አሲድ (ወይም አስፒሪን) በ1897 በጀርመናዊው ኬሚስት ፌሊክስ ሆፍማን ባቫሪያ ውስጥ ተቀመመ እና ለመድሐኒትነቱ በሔይንሪኽ ድሬሰር ተሞከረ፡፡ በ1899 ምርቱ ተጀመረ እና በ1900 የመጀመሪያዎቹ እንክብሎች ተሸጡ፡፡ አስፒሪን ከሳሊክሊክ አሲድ ይልቅ ጥቂት የጎን-ውጤቶች ብቻ ስለነበሩት ወዲያውኑ ተፈላጊ ሆነ፡፡ በኢንዱስትሪ ደረጃ ለመመረት የመጀመሪያው መድሐኒት የሆነው አስፒሪን ዛሬም በገፍ እየተፈበረከ ነው፡፡ አስፒሪን የልብ ድካምን በመከላከል ረገድ ጠቃሚ ውጤቶች እንዳሉት እስከተደረሰበት እስከ 1980ዎች አጋማሽ ድረስ በዋናነት የሚወሰደው ለራስ-ምታት ማስታገሻነት ነበር፡፡ አሴቲልሳሊክሊክ አሲድ ኮርቲዞን በ1940ዎች ውስጥ ስለ ኩላሊት እጢ ሽፋን (adrenal gland cortex) የተካሄዱ ጥናቶች አንዳንድ በተፈጥሮ የሚከከሰቱ ነቅአ-ዘሮች (hormones) [ስቴሮይድ ተብለውም ይጠራሉ] ፀረ-ብግነት ንብረቶች እንዳሏቸው ለይተው አስቀመጡ፡፡ በ1936 ለመጀመሪያ ጊዜ ከተፈጥሯዊ ምንጩ ተለይቶ የወጣው ኮርቲዞን ቆየት ብሎ በ1948 በአሜሪካዊው ሊዊስ ሄስቲንግስ ሳሬት ተቀመመ፡፡ ለደም-ስር ሪህ (rheumatoid arthritis) ባለው ተአምራዊ አስታጋሽነቱ ምክንያት በቀጣዩ ዓመት ለገበያ ተፈበረከ፡፡ ከእዚሁ ጋር ተያይዘው የተደረጉ ክሊኒካዊ ጥናቶች እናዳሳዩት፣ ኮርቲዞን ሪህን ባይፈውስም እና ብርቱ የጎን-ውጤቶች ቢያስከትልም ቅሉ፣ ለአስም እና ለአለርጂ ሕክምና ተጨማሪ ጥቅሞች ነበሩት፡፡ የስቴሮይድ ትንታኔ ተጨማሪ ጥናቶች ያነሰ የጎን-ውጤቶች ወዳሏቸው የተሸሉ ፀረ-ብግነት መድሐኒቶች ወደ ፕሬድኒሶን፣ ፕሬድኒሶሎን እና ዴክሳሜታዞን ፈጠራ አመሩ፡፡ ሊዊስ ሄስቲንግስ ሳሬት በአንጓ ብግነት ሳቢያ የተቆለመሙ ጣቶች

  2. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫.2 የሥነ-ልቦናዊ-ሕክምና (psychotherapeutic) መድሐኒቶች ክሎርፕሮማዚን ክሎርፕሮማዚን (ቶራዚን፣ ሂቤርናል) በመነሻነት እንደ ፀረ-አለርጂ መድሐኒት ከተፈጠረ በኋላ በ1954 የስሜት-መረበሽን (schizophrenia)ን ለማከም ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ ይህ አዲስ መድሐኒት በአስደናቂ ውጤቱ የተረጋገጠለት እና ለዘመናዊ ፀረ-ቅወሳ (antipsychotic) ሕክምና ፈር-ቀዳጅ ለመሆን በቃ፡፡ ወዲያውኑ የአእምሮ ሕመምን በሕክምና መቆጣጠር የኤሌክትሪክ-ንዝረትን (electroshock)፣ የኢንሱሊን ንዝረትን እና ፕሪፍሮንታል ሎቦቶሚን (የአንጎልን የፊት ክፍል ንፍቀ-ክበባት በቀድዶ-ሕክምና ማለያየትን) የመሳሰሉትን የቀድሞ የማከሚያ ዘዴዎችን ተካ እና በስፋተ-ዓለም ደረጃ የተቋማዊ ሕክምናን አሠራር ለመቀነስ ረዳ፡፡ በኋላ የተከናወነ ምርምር ደግሞ የክሎርፕሮማዚንን መድሐኒታዊ ሥነ-አሠራር ደረሰበት እና ሃሎፔሪዶልን እና ኦላንዛፓይንን ለመሳሰሉ ሌሎች በርካታ ፀረ-ቅወሳ (antipsychotic) መድሐኒቶች ቅመማ እንደ መሠረት አገለገለ፡፡ የአእምሮን ሕመም አጥፊ ውጤቶች ከሚያሳየው One Flew Over the Cuckoo’s Nest(1975) ከተባለው ፊልም የተወሰዱ ምስሎች ትራይሳይክሊክ ፀረ-ድብርቶች በመጀመሪያ እንደ ፀረ-ቅወሳ (antipsychotic) መድሐኒት በተቀመመው በኢሚፕራሚን ላይ በ1958 የተካሄደው ክሊኒካዊ ጥናት የመድሐኒቱን ፀረ-ድብርት ንብረቶች ይፋ አወጣ፡፡ መድሐኒቱ ውጤት የሚሰጠው አንጎል ውስጥ አነቃቂ መድሐኒቶችን የሚያስተላልፉትን ነርቫዊ-አስተላላፊዎችን (neurotransmitters) አሠራር በማቀላጠፍ ነው፡፡ በቀጣይነት በእዚህ መደብ ውስጥ የተቀመሙት በርካታ መድሐኒቶች በጥቅሉ 'ትራይሳይክሊክ 'ፀረ-ድብርቶች ተብለው ይታወቃሉ፡፡ በእዚህም ትራይሳይክሊክ ፀረ-ድብርቶች ለአእምሮ መቃወስ ማከሚያ መደበኛ መድሐኒቶች ሆኑ፡፡ ከምጥ በኋላ የመጎሳቆል ክስተት ቤንዞዲያዜፓይንስ በ1959 ክሎርዲያዜፖክሳይድ (ሊብሪዩም) ብቁእ የሆኑትን አዳዲሶቹን ፀረ-ጭንቀት (anti-anxiety) መድሐኒቶች፣ ቤንዞዲያዜፓይንስ ለመቀመም አስቻለ፡፡ ይህ መድሐኒት እና ከእርሱ የተወሰዱት ንጥሮች በ1950 የተገኙትን በአማካኝ ስኬታማ የነበሩትን አንክሲኦሊቲክ መድሐኒቶችን ባርቢቱሬትስን እና ሜፕሮባሜትን በፍጥነት ከተኩ ወዲህ የዘመናችን እጅግ ስኬታማ መድሐኒቶች ሆነው ይቆጠራሉ፡፡ በጣም መልካሞቹ እና አስተማማኞቹ ቤንዞዲያዜፓይንስ እንደ ሰመመን-ማስያዣ (hypnotic) መድሐኒቶች፣ ጡንቻ አፍታቺዎች እና የሚጥል በሽታ ማከሚያዎች ጭምር ስኬታማም ናቸው፡፡ ነርቫዊ-አስተላላፊዎች በአንጎል ውስጥ

  3. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫.3 ነቅአ-ዘሮች እና የነቅአ-ዘር ማስተካከያዎች ኢንሱሊን በቆሽት ልዩ ሕዋሳት የሚመረተው የፕሮቲን ነቅአ-ዘር (hormone)፣ ኢንሱሊን በሰውነት ውስጥ የደም ስኳርን (glucose) መጠን የሚቆጣጠር ነው፡፡ የኢንሱሊን አለመኖር እስከ 1920ዎች መባቻ ድረስ እንደ ገዳይ በሽታ ይቆጠር ወደነበረው ወደ ዓይነት 1 የስኳር-በሽታ ነው የሚያመራው፡፡ ሁለቱ ወጣት ካናዳዊያን ዶክተሮች፣ ፍሬዴሪክ ባንቲንግ እና ቻርልስ ኤች. ቤስት በ1921 ከአመስኳች እንሰሳት ቆሽት ያገኙትን ንጥር ለይተው እና አጽድተው በማውጣት አዲስ በመርፌ ተወጊ መድሐኒት ሠሩ፡፡ የዶክተሮቹ የመጀመሪያ ታካሚ ለመሞት የተቃረበው የ14-ዓመት ወጣት ከጥቂት ሣምንታት በኋላ ተሽሎት ከሆስፒታል ወጣ፡፡ ኢንሱሊን በኢሊ ሊሊ እና ኩባንያው በ1922 ከአመስኳች እንሰሳት ቆሽት ተፈበረከ፡፡ በዘረ-መል ሰንጥቆ-መተካካት (recombinant DNA) ቴክኖሎጂ ምሕንድስና በመጠቀም ከሰብአዊ ምንጮች የተሠራው የመጀመሪያው ኢንሱሊን በ1982 ተመረተ፡፡ የፍሬዴሪክ ባንቲንግ እና የቻርልስ ኤች. ቤስት ሥዕል ቴስቶስቴሮን ቴስቶስቴሮን ለተባእት ወሲባዊ ብልቶች እና ለሁለተኛ-ደረጃ ወሲባዊ ባሕሪያት ልማት ኃላፊ ነው፡፡ በመዋቅር ከኮሌስቴሮል ጋር የሚመሳሰል የስቴሮይድ ነቅአ-ዘርም ነው፡፡ ቴስቶስቴሮን በ1935 በመጀመሪያ ከኮሌስቴሮል የተቀመመው የነቅአ-ዘር (hormone) ጉድለት በሽታዎችን ለማከም ነበር፡፡ ቴስቶስቴሮን ከተፈጥሮ የሚገኙ ቁሶችን በኬሚካዊ እና በማይክሮባዮሎጂያዊ ዘዴዎች በመለወጥ ሊመረት ይችላል፡፡ ፕሮጄስቲኖች፣ ኤስትሮጂኖች እና አፍአዊ የወሊድ-መቆጣጠሪያዎች በ1930ዎች ውስጥ ሁለት አንእስታዊ ነቅአ-ዘሮች (hormones) ተለይተው ታወቁ እና ከተፈጥሯዊ ምንጮች ተመረቱ፡- ከእርጉዝ ባዝራዎች ሽንት እና ከሜክሲኮ ጣፈጭ ስር፡፡ ፕሮጄስቲኖች (ፕሮጄስቴሮን፣ የወር-አበባ ዑደት ነቅአ-ዘር [luteal hormone]) እርግዝናን እንደሚጠብቁ ሲደረስባቸው፣ ኤስትሮጂኖች (ፈሳሽ-አመንጪ ዕጢ ነቅአ-ዘሮች [follicular hormones]) የታወቁት ደግሞ በወር-አበባ ዑደቶች ነኪነታቸው ነበር፡፡ በ1950ዎች ውስጥ እነዚህ ነቅአ-ዘሮች በረጋ-ሠራሽነት ተመረቱ እና በሰው ጽንሰት እና በእርግዝና ላይ ያሏቸው ውጤቶች ተጠኑ፡፡ የእነዚህ መድሐኒቶች አስደማሚ የእርግዝና ተቆጣጣሪነት ጥራቶች ለሴቶች አፍአዊ የእርግዝና መቆጣጠሪያዎች (የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች) እንዲመረቱ አደረጉ፡፡ በ1960 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለገበያ የቀረበው ኤኖቪድ ለከፍተኛ ውጤታማነት የኤስትሮጂኖችንእና የፕሮጄስቲኖችን ድብልቅ የያዘ የመጀመሪያው የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ነበር፡፡ ፫.4 ጨጎ-አንጀት (gastro-intestinal) መድሐኒቶች የጨጓራ-ብግነት (ulcer) ሕክምና አመጣጥ ስኮትላንዳዊው ፋርማኮሎጂስት ጀምስ ብለክ እና ስሚዝ፣ ክላየን እና ፍሬንች የሚገኙ ባልደረቦቹ ሆድ'ቃ ውስጥ ከልክ ያለፈ የአሲድ ርጭትን ምንነት በ1972 ደረሱበት፡፡ የእዚህ ዓይነቱ ፋርማኮሎጂያዊ ምርምር በአሁኑ ወቅት የሚታወቀው “ምክንያታዊ የመድሐኒት ቅየሳ“ ተብሎ ነው፡፡ በ1976 እነዚሁ ተመራማሪዎች ከአነስተኛ የጎን-ውጤቶች ጋር የጨጓራን የአሲድ ርጭት የሚገታውን ሲሜቲዳይን (ታጋሜት) የተባለውን መድሐኒት ሠሩ እና የመድሐኒቱ በሰፊው ጥቅም ላይ መዋል ለጨጓራ ብግነቶች (gastric ulcers) የቀድዶ-ሕክምናን አስፈላጊነት በእጅጉ ቀነሰው፡፡ ታጋሜት ወዲያውኑ ተዝወትሮ የሚታዘዝ የመድሐኒቶች ቁንጮ ሆነ፡፡

  4. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫.5 የሕክምና ምርመራ እና የበሽታ ትንተና የሕክምና ምስል ቴክኖሎጂዎች በተገኙበት ጊዜ ስር-ነቀል ለውጦች ያመጡት የራጂ ማሺኖች እና MRI (መግነጢሳዊ ድምጽ-አጉዪ ምስል) አሳዪዎች (scanners) ዛሬ የሕክምና ምርመራ እና ክብካቤ ተዝወታሪ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ራጂን በ1895 ያገኘው ጀርመናዊ የሥነ-አካል-ሊቅ (ፊዚሲስት) ቪሊሄልም ኮንራድ ሮኤንትገን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳየው ምስል የሚስቱን እጅ አጥንቶች ነበር፡፡ በ1900 እያንዳንዱ ከፍተኛ ሆስፒታል የራሱ የራጂ ማሺን ነበረው፡፡ የኑክሌር መግነጢሳዊ ድምጽ-አጉዪ (NMR) ቴክኖሎጂ በ1970ዎች ውስጥ ኬሚካዊ መዋቅሮችን ለመወሰን ጥቅም ላይ ሲውል፣ በ1985 ደግሞ መግነጢሳዊ ድምጽ-አጉዪ ምስል አሳዪዎች ለሰው-ልጅ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተፈቀደ፡፡ ኬሚካዊ ማነጻጸሪያ አላባዎች እና ልዩ የፊልም ብርሃን ተቀባይ ልባሶች (emulsions) የራጂን፣ CT (መጠነ-ሦስት የራጂ ምስል፣ ኮምፒዩተራዊ አነጣጥሪ) አሳዪዎችን፣ ብሎም የ MRIን እና የልዕለ ድምጽ ምስሎችን አሻሻሉ፡፡ በብርሃን የተላለፉት የወይዘሮ ሮኤንትገን እጅ አጥንቶች ሕክምናዊ አይዞቶፖች ሕክምናዊ ምስል የሁንጋሪያዊውን የኖቤል ሎሬት ጊዮርግ ሂቪሴይን (1943) ፈር-ቀዳጅ ሥራ ተከትሎ የውስጣዊ ብልቶችን አሠራር ለመወሰን በአብዛኛው የተረዳው በሕክምናዊ አይዞቶፖች በመጠቀም ነበር፡፡ በ1935 ሂቪሴይ በሬዲዮአክቲቭ አስኳሎች (nuclides) በመጠቀም የፎስፎር ስልቀጣን (metabolism) አሠራር ወሰነ፡፡ ውህዶች (technetium-99mን እና thallium-201ን በመሳሰሉ) በሬድዮአክቲቭ አይዞቶፖች ወይም (bariumን እና የiodine ውህዶችን በመሳሰሉ) በሬድዮ ኦፔኮች ይሸፈናሉ፡፡ ከእዚያም እነዚህ በሬዲዮ የተሸፈኑ ውህዶች የተላኩባቸውን ብልቶች ጠቃሚ ምስሎች እንዲያሳዩ በጋማ-ፈልጎ-አግኚ ካሜራዎች አማካኝነት ሰውነት ውስጥ ይለቀቃሉ፡፡ የሕክማናዊ አይዞቶፖች ጥቅሞች እጢን ፈልጎ-ማግኘት፣ የጉበት በሽታን ማሳወቅ እና ለልብ አሠራር የጭንቀት ምርመራን ያካትታሉ፡፡ የኬሚካዊ መሞከሪያዎች ልማት ዛሬ ሕክምናዊ ሁኔታዎችን የምንወስነው በደም፣ በሽንት፣ በሰገራ፣ በምራቅ እና በላብ ውስጥ በኬሚኮች ተፈልገው ሊገኙ የሚችሉ የበሽታ አመላካቾችን ወይም የመድሐኒት ዝቃጮችን በማጥናት ነው፡፡ የቤተ-ሙከራ ፍተሻ፣ ረቂቅ በኮምፒዩተር-ተረጂ የመተንተኛ መሣሪያዎች እና የውስጠ-ቤት መመርመሪያዎች ሁሉ መሠረታዊ ኬሚካዊ አጸፋዎችን ይለካሉ፡፡ በ19ኛው ምእት-ዓመት መባቻ አካባቢ የምርመራ ውጤት የሚመሠረተው ክሊኒካዊ ምልክቶችን በመታዘብ ነበር፡- አንድ ታካሚ ለውሱን-በሽታ ሕክምና አዎንታዊ አጸፋ ካሳየ/ች እርሱ/ሷ ያ በሽታ አለበት/ባት ብሎ ለመወሰን፡፡ የበሽታ ምርመራ ፍተሻ በ1882 የተጀመረው ፖል ኤህርሊኽ (በአንዳች አቅላሚ ተለይቶ የሚታወቅ) የተስቦ ባክቴሪያ (typhoid bacillus) ሲገኝ ብቻ የምርመራው ውጤት ተስቦ መሆኑን ባረጋረጠ ጊዜ ነበር፡፡ ከእዚያ በፊት ግን የተስቦ በሽታ ምርመራ የተመሠረተው በታካሚው የቆዳ ቀለም ላይ ነበር፡፡ የግል ክትትል አመጣጥ በቀላሉ የተዘጋጁ የውስጠ-ቤት የመመርመሪያ ማሲኖዳዎች (kits) የሰውን ጤንነት በግል ለመከታተል ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ፡፡ ለምሣሌ፣ የስኳር-በሽታ ሕሙማን በሽንታቸው ውስጥ ስኳር መኖሩን ለመወሰን በግድ ወደ አንድ ቤተ-ሙከራ መሄድ ነበረባቸው፡፡ በ1941 “ማይልስ ላቦራቶሪስ“ የመጀመሪያውን መደበኛ የውስጠ-ቤት ስኳር-በደም-ውስጥ መፈተሻ አስተዋወቀ፡፡ ለማልማት አስቸግረው የነበረ ይሁን እንጂ፣ ክተት-እና-አንብብ የሽንት መመርመሪያዎች በ1956 ተሠሩ፡፡ በ1960ዎች ውስጥ የስኳር ሕሙማንን ጤንነት የሚታደገው እና ተፈጥሯዊ-ስኳርን (glucose) ፈልጋገው ከሚያገኙ ኬሚካዊ ስንጥሮች ጋር የሚሠራው የመጀመሪያው በእጅ-ተያዥ እና በባትሪ-ተንቀሳቃሽ የደም ተፈጥሯዊ-ስኳር መለኪያ በይፋ ወጣ፡፡ በ1970ዎች እና 1980ዎች ውስጥ ለሰገራ ስውር ደም (fecal occult blood)፣ ለእንቁላል መመረት (ovulation)፣ ለእርግዝና እና ለቁልምም ባክቴሪያ (strep) የውስጠ-ቤት መመርመሪያ ማሲኖዳዎች ተዋወቁ፡፡

  5. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫.6 ፀረ-በሽታ-አስተላላፊ መድሐኒቶች ሳልቫርሳን እናፕሮንቶሲል ጀርመናዊው ባክቴሪዮሎጂስት፣ ፖል ኤህርሊኽ ስለ አርሴኒክ ውህዶች ፀረ-ባክቴሪያ ንብረቶች አጠና እና በወሲብ ለሚተላለፈው አደገኛ በሽታ፣ ቂጢኝ ስኬታማ ሕክምና በ1909 ሳልቫርሳንን ፈለሰፈ፡፡ ይህንኑ ፈለግ የተከተሉ ሌሎች ተመራማሪዎች ደግሞ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን የሚወጉ ንቁእ ውህዶች አገኙ፡፡ ኬሚስቶች ስር-ለሰደደ የሣምባ-ምች (ኒሞኒያ) መንስኤ የሚሆነውን ገዳዩን ስትሬፕቶኮካል ተላላፊ-በሽታ ለመፈወስ የሚያስችል አንድ ፀረ-ባክቴሪያ መድሐኒት ሲፈልጉ ቀድሞ ለጨርቃ-ጨርቆች ማቅለሚያነት ጥቅም ላይ ይውል የነበረው የመጀመሪያው ሱልፋ መድሐኒት፣ ፕሮንቶሲል በ1932 ታወቀ፡፡ ይህ ግኝት ፋይዳው እጅግ የጎላ በመሆኑ ጀርመናዊው ባዮኬሚስት፣ ጌርሃርድ ዶማግ በእዚህ መስክ ውስጥ ላከናወነው ሥራ በሕክምና የ1939ን የኖቤል ሽልማት ተቀበለ፡፡ ቆየት ብሎም የፕሮንቶሲል ንቁእ ፀረ-ባክቴሪያ አላባ ሱልፋኒላማይድ መሆኑ ተደረሰበት፡፡ ከእዚያ በኋላ የ1938ን ሱልፋፒሪዳይንን ጨምሮ ብዙ ሌሎች ፀረ-ባክቴሪያዎች (antibiotics) ከእዚሁ አላባ ተፈጠሩ፡፡ እነዚህ የሱልፋ መድሐኒቶች በ1940ዎች ውስጥ የሣምባ ምችን ገዳይነት በመቀነስ ረገድ ድንቅ ስኬታማ ውጤት በማሳየት የሚሊዮናትን ሕይወት ታደጉ፡፡ ነገር ግን የፔኒሲሊን ዘመን ሲብት የእነዚያ መድሐኒቶች ፋይዳ አሽቆለቆለ፡፡ ስትሬፕቶኮከስባክቴሪያ ጌርሃርድ ዶማግ ፕሮንቶሲል አሌክሣንደር ፍሌሚንግ ፔኒሲሊን ስኮትላንዳዊው ባክቴሪዮሎጂስት፣ አሌክሣንደር ፍሌሚንግ በተፈጥሮ ከሚከሰት ሻገት (ፔኒሲሊዩም ኖታቱም) ነጥሎ ያወጣወን ባክቴሪያ ለመግደል የሚችል እምቅ-ኃይል ያለው ንጥረ-ነገር በ1928 አገኘ፡፡ በ1943 ሰፊ የጦርነት-ጊዜ ውጥን በተዘረጋበት ወቅት በእዚህ ተፈጥሯዊ ንጥረ-ነገር ላይ ተመሥርቶ የተፈጠረው ፔኒሲሊንበ፪ኛው የዓለም ጦርነት የቆሰሉ ብዙ አሜሪካዊያን እና ብሪታኒያዊያን ወታደሮችን ከተላላፊ በሽታዎች እና ከአካል መቆረጥ በመታደግ ድንቅ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገቡ አይዘነጋም፡፡ ያ ተፈጥሯዊ ፔኒሲሊን በዋጋው ውድ እና እንደ ልብ የማይገኝ ስለነበር ታክመው ከዳኑ ታካሚዎች ሽንት ተነጥሮ እንደገና መመረት ነበረበት፡፡ ኬሚስቶች አዲስ የቅመማ ዘዴ ሞከሩ፡- መድሐኒቱ የተመሠረተበትን ተፈጥሯዊ ንጥረ-ነገር በሰው-ሠራሽነት ለማምረት፡፡ እንዲቀመም ያስቻለው የፔኒሲሊን ኬሚካዊ መዋቅር በ1940ዎች ውስጥ የታወቀው በብሪታኒያዊው ተመራማሪ በዶሮቲ ክራውፎርድ ሆጅኪን ነበር፡፡ በ1957 በርካታ መድሐኒት አምራች ኩባንያዎች ይህንን መድሐኒት ቀመሙ እና አምርተው ለገበያ አቀረቡ፡፡ ይህም ስኬት ነበር ዘመናዊ ፀረ-ባክቴሪያ ሕክምና መጀመሩን ያበሰረው፡፡ ፔኒሲሊዩም ኖታቱም ዚዶቩዳይን (AZT) ዚዶቩዳይን (AZT) ሰብአዊ የተፈጥሮ-መከላከያ-አጉዳይ ቫይረስን (HIV) ለማከም ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተፈቀደው በ1987 ነበር፡፡ መድሐኒቱ በመጀመሪያ በ1964 ይቀመም እንጂ፣ ለካንሰር ኬሚካዊ ሕክምና ውጤተ-ቢስ ነበር፡፡ በአንድ የአሜሪካዊያን ተመራማሪዎች ቡድን ፀረ-ኤይድስ-አማጭ-ቫይረስነቱ (retroviruses) እስከታወቀበት እስከ 1986 ድረስ ምርምሩ ተቋርጦ ነበር የቆየው፡፡ AZT እና ተዛማጅ ኒዩክሊዩሳይድ መድሐኒቶች ውሱን ቫይረሳዊ ኢንዛይሞችን ዒላማ በማድረግ ለመግታት ይችላሉ፡፡ በመጀመሪያ በAZT እንደታየው የHIV መድሐኒት ተቋቋሚነት በፍጥነት በመከሰቱ ምክንያት የHIVን ተላላፊነት ለማከም ከእንግዲህ በሌጣ-መድሐኒት (mono-drug) ሕክምና ለመጠቀም አልተቻለም፡፡ ዚዶቩዳይን ክሪስታሎች ዚዶቩዳይን

  6. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫.7 የልበ-ደም-ጋናት (cardiovascular) አስተካከም የልብ አመታትን ማስተካከል የልብ ምትን በማስተካከል ረገድፕሮኬይን የውሱን አካባቢን ሕመም ለማስታገስ (ፀረ-ኢመደበኛ የልብ ምትም ይባላል) ያለው ችሎታ የታወቀው በ1930ዎች ውስጥ ነበር፡፡የእዚህ ዓይነቱ መድሐኒት ሕክምና ውስብስብ ከመሆኑም ሌላ፣ ኢመደበኛ የልብ ምትን የሚገቱ መድሐኒቶች በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ለራሱ ለኢመደበኛ የልብ ምት መንስኤ ሊሆኑ ስለሚችሉ አስቸጋሪም ናቸው፡፡ ፕሮኬይን ለእዚህ ጥቅም እንዲውሉ ከተፈቀደላቸው የመጀመሪያ መድሐኒቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡ ፕሮኬይን የሕዋስ ስስ-ሽፋን ፕሮቲኖችን (ሶዲየም ቻነልስ ተብለውም ይታወቃሉ) የሚገታ ነው፡፡ ፕሮኬይን ን ተከትሎ ቤታ-ብሎከርስን እና ፖታሺየም ወይም ካልሺየም ቻነል አንታጎኒስትስን የመሳሰሉ በርካታ መድሐኒቶች ተሠሩ፡፡ የልብ መቆምን ማከም በበርካታ እጽዋት ውስጥ በተፈጥሯዊነት የሚገኙት ውህዶች ቡድን የሆኑት ዲጂታሊስ ግላይኮሳይድስ የልብ መቆምን ለማከም ለምእታተ-ዓመታት ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር፡፡ እነዚህ ውህዶች የልብ አመታትን ኃይል እንዴት እንደሚጨምሩ በምርምር ተለይቶ ከታወቀ በኋላ ዲጎግሲን ከግሬሺያን ፎክስግሎቭ (ዲጂታሊስ ላናታ) ቅጠሎች ተቀመመ እና ለተዛባ የልብ ምት (atrial fibrillation) እና ለልብ ደም መልስ መታፈን (congestive heart failure) ሕክምና እንዲውል በ1954 ተፈቀደ፡፡ ለስቆም ፀረ-ክፍተኛ-የደም-ግፊት መድሐኒቶችም የልብ መቆምን ጭምር ለማከም እንደሚጠቅሙ ተደረሰበት፡፡ የደም መቆጣጠርን መግታት በ1935 የደም ዝውውር ሲደረግ ከእንሰሳት ጉበት የተቀመመው ተፈጥሯዊ ምርት፣ ሄፓሪን በመጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው ትሮምቦሲስን (የደም መቆጣጠርን) ለማከም ሲሆን፣ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ የወል ጥቅም የሚሰጥ ፀረ-ቁጥረት (ደም አቅጣኝ ተብሎም ይታወቃል) ሆነ፡፡ ሄፓሪን፣ ከእዚህም በተጨማሪ፣ በልብ እና በዋና የደም-ስሮች ቀድዶ-ሕክምና ጊዜም የደም መቆጣጠርን የሚከላከል ነው፡፡ የደም ስርጭት መገታትን (strokes) የሚከላከለው፣ ብሎም የልብ ድካምን እና ትሮምቦሲስን የሚያክመው ዋፋሪን (ኩማዲን) ደግሞ በ1955 ተፈቀደ፡፡ በ1970ዎች ውስጥ ደግሞ ደም ከተቆጣጠረ በኋላም ቢሆን በትሮምቦሊቲክስ (በፀረ-ደም መቆጣጠሪያ መድሐኒቶች) ሊታከም እሚችል ታወቀ፡፡ የደም መቆጣጠርን ለማሟት በኤንዛይም በመጠቀም በተራው ወደ ዩሮኪናዜ (1977)፣ ስትሬፕቶኪናዜ (1978) እና በዘረ-መል ምሕንድስና ወደተሠራው ድቅል ፕላዝሚኖጂን አነሳሹ tPA (1987) አመራ፡፡ የደም ስብ (cholesterol) ደረጃዎችን መቆጣጠር በደም-ስሮች (arteries) ውስጥ የስብ ክምችቶች መበራከት (አርቴሪዮስኬሌሮሲስ) የደም-ቅዳ-ደም-መልስ (coronary) ልብ በሽታ እና የደም ስርጭት መገታትቶች (strokes) ዋና መንስኤ ነው፡፡ አንድ አስጊ ኤንዛይም በኮሌስትሮል ሕያው-ቅመማ (biosynthesis) ከመነሻው እና ከመጠን-ወሣኝ ደረጃው ወደ ሜቫሎኔት መለወጡን በመግታት የደም ስብ ደረጃዎችን (hypolipemic activity) የሚቆጣጠረው ሎቫስታቲን (ሜቫኮር ) በ1987 ነበር የጸደቀው፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ሲምቫስታቲንን እና አቶርቫስታቲንን የመሳሰሉ የበለጠ እምቅ-ኃይል ያላቸው መድሐኒቶች በደም ውስጥ ከልክ በላይ የተጠራቀሙ ስቦችን (hyperlipidemia) በውጤታማነት እና በአስተማማኝነት በማከም ረገድ ስር-ነቀል ለውጥ አመጡ፡፡ አርቴሪዮስኬሌሮሲስ

  7. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫.8 የካንሰር ኬሚካዊ-ሕክምና የካንሰር ኬሚካዊ-ሕክምና (chemotherapy) አመጣጥ ካንሰርን ለማከም በኬሚካሎች መጠቀም (cancer chemotherapy) በሉዊስ ኤስ. ጉድማን እና በአልፍሬድ ጊልማን አማካኝነት በናይትሮጂን ሰናፍጮች ክሊኒካዊ አጠቃቀም የተጀመረው በ1942 ነበር፡፡ በእዚያው ወቅት ፎሊክ አሲድን (antimetabolites ተብሎም ይጠራል) የሚገቱ መድሐኒቶች ጭምር ተሠሩ፡፡ አሚኖፕቴሪን (1947) ሉኬሚያን (የደም ካንሰርን) ለማከም ውጤታማ የነበረ ቢሆንም ቅሉ፣ በነጭ የደም ሕዋሳት ላይ በሚያስከትላቸው አሉታዊ ውጤቶቹ ሳቢያ በአስቸኳይ በሜቶትሬዜት እንዲተካ ተደረገ፡፡ ጆርጅ ሂቺንግስ እና ቻርለስ ሃይድልበርገር በ1950ዎች ውስጥ አንቲሜታቦሊቲክ ሜርካፕቶፑራይንን ለደም ካንሰር፣ ብሎም ፍሉኦሮኡራሲልን ለጨጎ-አንጀት (gastrointestinal) እና ለጡት እጢዎች ማከሚያ ቀመሙ፡፡ ፀረ-ሕዋስ-ክፍፍል (ሳይቶቶክሲክ) መድሐኒቶች ሳይቶቶክሲክ መድሐኒቶች (ወይም ለሕዋሳት መርዛማ የሆኑ መድሐኒቶች) የተቀመሙት ከእጽዋት ሲሆን፣ ለካንሰር ኬሚካዊ-ሕክምና በመጀመሪያ የተዋወቁት ደግሞ በ1963 ነበር፡፡ እነዚህ ፀረ-ካንሰር መድሐኒቶች የሚሠሩበት መርሕ ኒኦፕላስቲክን (ወይም ካንሰራዊ ሕዋሳትን) የመሳሰሉ ሕዋሳትን በፍጥነት ማባዛት በሳይቶቶክሲክ መድሐኒቶች ይበልጥ እንዲበላሹ ያደርጋል የሚል ነው፡፡ ከበርካታ አማራጮች መካከል ከባሕር እጽዋት እና ከፖዳፊሎቶክሲን በ1970 ውስጥ የተቀመሙት ቪንካ አልካሎይድስ (ቪንክሪስታይን እና ቪንብላስታይን) ይገኛሉ፡፡ ታክሶል በ1971 ከፓስፊኩ ይው ዛፍ ቅጠሎች ተነጥሮ ወጣ እና በ1990ዎች ውስጥ የተባባሰ የጡት ካንሰርን፣ ብሎም የሣምባ ካንሰርን ለማከም ተዘጋጀ፡፡ ታሞክሲፌን በ1971በረጋ-ሠራሽነት የተዘጋጀው ታሞክሲፌን በ1977 ሥራ ላይ የዋለው የኤስትሮጂን-ጥገኛ እጢዎችን እድገት በማዝገም የጡት ካንሰርን ለማከም ነበር፡፡ ከፍተኛ የኤስትሮጂን ደረጃዎች ሕዋስ ወደ ጡት ‘ማግ' (tissue) መዛመቱን ስለሚያፋጥኑ የካንሰር ሕዋሳት እድገትን ሊያነቃቃ የሚችለው የእዚህ ዓይነቱ ኬሚካዊ-ሕክምና ተፈጥሯዊ ነቅአ-ዘሮችን (hormones) ይገታል፡፡ ሜጌስትሮል በተመሳሳይ ሁኔታ የሚሠራ እና ለተደጋጋሚ የጡት እጢዎች ሕክምና ጥቅም ላይ የሚውል በተፈጥሮ ከሚከሰት ስቴሮይድ ነቅአ-ዘር፣ ፕሮጄስትሮን በረጋ-ሠራሽነት የሚገኝ መድሐኒት ነው፡፡ በራጂ የተነሳ የጡት እጢ ምስል የጡቶችን ሁኔታ በግል መከታተል የምርመራ ውጤቱ ቀደም ብሎ እንዲታወቅ የሚያደርግ ነው፡፡

  8. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ ፫.9 ድንቅ የጤና ክብካቤ ቁሶች ሰው-ሠራሽ እጅ/እግር እና ሕክምናዊ ማቀላጠፊያዎች ዘመናዊ ሰው-ሠራሽ እጅ/እግር እና ብልቶች፣ ተተኪ አንጓዎች፣ ተለጣፊ ሌንሶች እና የማዳመጫ መሣሪያዎች፣ ብሎም ከልዩ ፕላስቲኮች እና ከሌሎች ከፍተኛ ቴክኒክ-ወለድ ቁሶች የሚሠሩ ሕያው-ቁሶች (biomaterials) ሁሉ የተመረቱት በኬሚስትሪ አማካኝነት ነው፡፡ ኬሚስቶች እና መሐንዲሶች የሞሊኪዩሎችን መዋቅሮች በመቆጣጠር እና አዳዲሶችንም በመፍጠር ጠንካራ፣ ተጣጣፊ እና ለረጅም የሚቆዩ አዳዲስ የሕክምና ቁሶችን ሠርተዋል፡፡ ከእነዚህ ሕክምናዊ ማሳለጫዎች መካከል ጥቂቶቹ የ1945 ሰው-ሠራሽ ኩላሊት፣ የ1950ዎቹ ሰው-ሠራሽ የልብ አፎቶች (valves) እና በ1982 በቀድዶ-ሕክምና የተደረገው ቋሚ የሰው-ሠራሽ ልብ ተከላ ናቸው፡፡ በ1956 ፕላስቲክ ተለጣፊ ሌንሶች የተዋወቁ ሲሆን፣ በ1985 ደግሞ ለስላሳ ባለ ክልኤ-እይታ (bifocal) ተለጣፊዎች ተሻሽለው ተሠሩ፡፡ ሰው-ሠራሽ የልብ አፎቶች ሰው-ሠራሽ ልብ ሕክምናዊ መሣሪያዎች በዛሬዎቹ ሆስፒታሎች እና የጤና ክብካቤ ኪሊኒኮች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉትን ፕላስቲክ እና ቪኒል ሕክምናዊ ማሳለጨዎች ሁሉ ለመፈብረክ ከሞላ-ጎደል ትልቁን ሚና የተጫወተው ኬሚስትሪ ነው፡፡ የዛሬዎቹ ሕክምናዊ መሣሪያዎች ለእለታዊ ጥቅም ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ፣ ብሎም ንጹሕ፣ የመከነ እና ከጀርም ነፃ የሆነ ሥነ-ምሕዳር ለመፍጠር የሚረዱ መሆን አለባቸው፡፡ በርካታ ተደጋጋሚ ሕክምናዊ ሂደቶች የሚጠቀሙባቸው የዘመኑ የመመርመሪያ መሣሪያዎች፣ ስቴቶስኮፖች፣ መጠቅለያ ሻሾች (bandages) እና ሌሎች ድንቅ ድርማጎች (fabrics)፣ ሲሪንጆች፣ የቀድዶ-ሕክምና ማሳለጫዎች፣ የደም ከረጢቶች እና ፕላስቲክ አቅርቦቶች ሁሉ የሚመረቱት በኬሚስትሪ አማካኝነት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የሕጻናትን ስሱ ቆዳ ከብግነት የሚከላከሉት የንጽሕና መጠበቂያዎች እንኳ እርጥበት-መጣጭ (hygroscopic) ፖሊመሮች አሏቸው፡፡ ፀረ-ተውሳኮች (disinfectants) እና ማንጫዎች (bleaches) ኬሚስትሪ የመኖሪያ-ቤትዎን ንጽሕና ለመጠበቅ፣ ሻጋታን (mould) እና አጣቆን (mildew) ለማስወገድ፣ ብሎም እድፎችን ለማጥፋት የሚያስችል ነው፡፡ ኬሚስቶች በ1900ዎች መባቻ ውስጥ ባክቴሪያን ለመቆጣጠር እና ልብሶችን እና የመኖሪያ-ቤትን ለማጽዳት አትኩረው ነበር፡፡ በ1913 ተመራማሪዎች ለተደራሽ እና ለመጠቀም ቀላል ማንጫ አንድ ቀመር አወጡ፡፡ ማንጫዎች ዛሬ ቢሊዮናት ጀርሞችን እና ባክቴሪያዎችን ለማስወገድ የቤት ውስጥ መገልገያዎች ውጤታማ ፀረ-ተውሳኮች ናቸው፡፡ ክሎሪን ጭምር በመኖሪያ-ቤቶች፣ በሆስፒታሎች እና በሌሎች ሕንጻዎች ውስጥ በቫይረሶች እና በባክቴሪያዎች መንስኤነት ለሚመጡ በሽታዎች ማስወገጃ ኃያል መሣሪያ ነው፡፡ ሁንጋሪያዊው የማሕጸን-ሐኪም፣ ኢግናቲየስ ሴሜልዌይስ በ1847 በመምሪያው ውስጥ በክሎሪን ውሃ እጅን መታጠብ ለማስተዋወቅ ግንባር-ቀደሙ ነበር፡፡

More Related