1 / 5

፪.1 የመገናኛዎች ግስጋሴዎች

፪. የቴክኖሎጂ ችካሎች በመረጃ እና በመገናኛዎች ውስጥ. ፪.1 የመገናኛዎች ግስጋሴዎች. የስልክ መሠራት

bell
Download Presentation

፪.1 የመገናኛዎች ግስጋሴዎች

An Image/Link below is provided (as is) to download presentation Download Policy: Content on the Website is provided to you AS IS for your information and personal use and may not be sold / licensed / shared on other websites without getting consent from its author. Content is provided to you AS IS for your information and personal use only. Download presentation by click this link. While downloading, if for some reason you are not able to download a presentation, the publisher may have deleted the file from their server. During download, if you can't get a presentation, the file might be deleted by the publisher.

E N D

Presentation Transcript


  1. ፪. የቴክኖሎጂ ችካሎች በመረጃ እና በመገናኛዎች ውስጥ ፪.1 የመገናኛዎች ግስጋሴዎች የስልክ መሠራት ስልክ በ1876 በአሌክሣንደር ግርሃም ቤል ከተፈለሰፈ ወዲህ በዓለም ዙሪያ ከሞላ-ጎደል ፈጣን ግንኙነቶች በመስጠት ረገድ የዘመናዊ ሕይወት የመሠረት-ድንጋይ ነው የሆነው፡፡ የመጀመሪያው የሁለት-አቅጣጫ የድምጽ ውይይት በ1926 በአትላንቲክ ውቅያኖስ በኩል የተላለፈ ሲሆን፣ (በራዲዮ በመጠቀም) የመጀመሪያው ንግዳዊ የስልክ አገልግሎት ደግሞ በኒው ዮርክ እና በሎንዶን መካከል በ1927 ተሰጠ፡፡ ‹AT&T› በ1935 ዓለም-አቀፍ የስልክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ውቅያኖስ-ተሻጋሪ የስልክ አገልግሎት በባሕር-ጠለቅ ገመደ-ሽቦ በ1956 ሲዘረጋ፣ ከ1962 አንስቶ ደግሞ በመገናኛ ሳቴላይቶች እየተላለፈ ነው፡፡ ዛሬ ኬሚካዊ መሐንዲሶች ከመዳብ ሽቦ ወደ ፋይበር ኦፕቲክስ፣ ከመክፈቻ-ሠሌዳዎች (switchboards) ወደ ሳቴላይቶች እና ከሽቦ-መስመሮች ወደ በይነ-መረብ አሸጋግረውናል፡፡ ሽቦ-አልባ መገናኛዎች ተንቀሳቃሽ (cellular) ስልኮች እና መልእክት-ማስተላለፊያዎች (pagers) የሚመኩት በኬሚስትሪ በተፈጠሩ በታተሙ እና በተቀናጁ ስርኩዊቶች፣ በዘመኑ ቁሶች እና በሚጢጢ (miniaturization) ቴክኒኮች ላይ ነው፡፡ የ‹AT&T› አብያተ-ሙከራዎች በ1940ዎች ውስጥ ተንቀሳቃሽ የመኪና ስልኮች ይሥሩ እንጂ፣ በመገናኛ ቦዮች (channels) አለመኖር ሳቢያ እምብዛም አይፈለጉም ነበር፡፡ በ1980ዎች ውስጥ ስር-ነቀል እመርታ መጣ፡- የሚንቀሳቀሱ ጠሪዎችን ወዲያውኑ በማገናኘት እያንዳንዱ ሴል በድጋሚ ጥቅም ስንዲሰጥ ሽቦ-አልባ መገናኛዎችን ወደ ተከታታይ ሴሎች ከፋፍሎ በመመደብ፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በፍጥነት ተፈላጊ ሆኑ፡፡ ለተንቀሳቃሽ ስልኮች ዳግም-ተሞይ ሊቲየም-አየን ባትሪዎች በመፍጠር ረገድ አንድ ሚና የተጫወተውም ኬሚስትሪ ነው፡፡ መክፈቻ-ሠሌዳ የፎቶኮፒ ቴክኖሎጂ እና ዜሮግራፊ ጀርመናዊው ፈልሳፊ አርዘር ኮርን በ1902 የመጀመሪያዎቹን ምስሎች በኤሌክትሮኒካዊነት ቢያስተላልፍም ቅሉ፣ የመጀመሪያው ተግባራዊ የፋክስ ማሺን እውን የሆነው ግን በ1924 ነበር፡፡ ያ ማሺን በቴሌፎቶግራፊ በመጠቀም ምስልን ለማስተላለፍ በስልክ ስርኩዊቶች ነበር የተመቻቸው፡- የፎቶግራፍን ብርሃን- አስተላላፊነት (transparency) የምስሉን ጥላዎች ወደ‘ሚያመለክቱ ወደ ኤሌክትሪካዊ ምልክቶች በመለወጥ፡፡ ይህ መረጃ በስልክ አማካኝነት ወደ ተቀባይ የፎቶግራፍ ፊልም ከተላለፈ በኋላ ነበር በጨለማ-ክፍል ውስጥ የታተመው፡፡ በ1949 የአንድን ምስል እቅጩ ግልባጭ የሚያወጣው ዜሮግራፊያዊ ገልባጭ (copier) ተዋወቀ፡፡ በፎቶኮፒ ቴክኖሎጂ ረገድ የኬሚስትሪ ፈጠራዎች አዳዲስ ቶነሮችን እና ቀለሞችን፣ ረቂቅ የወረቀት ቴክኖሎጂን እና የኦርጋኒክ ፎቶሪሴፕተርስ ቴክኖሎጂን ጨምሮ በ1970ዎች ውስጥ ተዋወቁ፡፡ ቴሌፎቶግራፊ ሌዘር እና ፋይበር ኦፕቲክስ አሁን መረጃን በሌዘር-ርጭት ብርሃን ለማስተላለፍ ታሕታይ-መዋቅር የሚሆኑት የንጹህ መስተዋት ፋይበሮች ስር-ነቀላዊ የቴክኒክ ግኝቶች ናቸው፡፡ የመጀመሪያውን ኦፕቲካል ፋይበር በ1970 ውስጥ የፈለሰፉት ኬሚካዊ ተመራማሪዎች ነበሩ፡፡ ወዲያውኑ ፋይበር ኦፕቲኮች ተፈበረኩ እና እንደ ቅንጁ ተዳማሪዎች (integrated components) ተተከሉ፡፡ በመረብ-ሥራ አማካኝነት የድምጽ መረጃ እና የቪዲዮ አገልግሎት የሚሰጠው የመጀመሪያው የብርሃን-ሞገድ ሥርዓት በ1977 ተዘረጋ፡፡ ዛሬ አንድ ነጠላ የፋይበር ኦፕቲክ ገመድ ሚሊዮናት የስልክ ጥሪዎችን፣ የመረጃ ማኅደሮችን እና የቪዲዮ ምስሎችን ለማስተላለፍ ይችላል፡፡

  2. ፪. የቴክኖሎጂ ችካሎች በመረጃ እና በመገናኛዎች ውስጥ ፪.2 የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ የኮምፒዩተሮች እድገት ኪሚካዊ ምሕንድስና የኮምፒዩተር አብዮትን እያፋጠነ ኮምፒዩተሮችን ፈጣን፣ ይበልጥ ኃያል እና ይበልጥ ተደራሽ ማድረጉን እንደቀጠለ ነው፡፡ የመጀመሪያው ኤሌክትሮኒክ ኮምፒዩተር በ1939 በአዮዋ መስተዳድር ዩኒቨርስቲ ተፈለሰፈ፡፡ ጥንድ (binary) ቁጥሮች እና መስተጻምራዊ አመክንዮ (Boolean logic) ያላቸው መርሐ-ተገብሯዊ አስሊዎች (programmable calculators) በ1940ዎች ውስጥ መታየት ጀመሩ፡፡ በ1946 የመጀመሪያው ኤሌክትሮኒክ ዲጂታዊ ኮምፒዩተር፣ ENIAC በተግባር ላይ ዋለ እና በ1962 ደግሞ የመጀመሪያው ሚኒኮምፒዩተር ለገበያ ወጣ፡፡ በ1971 Intel ኩባንያ ታዋቂውን 4004 4-ቢት ማይክሮፕሮሴሰርን ለተጠቃሚዎች መጠቀሚያነት አስተዋወቀ እና የብል ኮምፒዩተር ገበያ ደራ፡፡ ዛሬም የትራንስስተሮች፣ የሲሊኮን ቺፕስ፣ የቅንጁ ተዳማሪዎች (integrated components)፣ የመረጃ ማከማቻ መሣሪያዎች እና የዘመኑ ቁሶች ፈጠራ እንደቀጠለ ነው፡፡ ጆን ፎን ኒዩማን እና ENIAC ENIAC ሴሚኮንዳክተር ቴክኖሎጂ ለዛሬዎቹ ኮምፒዩተሮች፣ ኤሌክትሪካዊ ዕቃዎች እና የመገናኛ መሣሪያዎች ኃይል ለመስጠት ሲሊኮንን እና ጀርማኒየምን ወደ ሴሚኮንዳክተሮች ለመለወጥ የሚያስችለው ኬሚስትሪ ነው፡፡ ሴሚኮንዳክተሮች፣ በብረታ-ብረቶች ተቃራኒ፣ ከፍ ባለ መጠነ-ሙቀት ኮንዳክቲቪቲን የሚጨምሩ የቁሶች አንድ ምድብ ናቸው፡፡ እነዚህ ሴሚኮንዳክተሮች የኤሌክትሮኖችን መትረፍረፍ ወይም እጥረት ለመፍጠርም ያስችላሉ፡፡ የኮምፒዩተር ቺፖች እና ቅንጁ ተዳማሪዎች ((integrated components) የሚሠሩት ከሴሚኮንዳክቲንግ ቁሶች ነው፡፡ ሴሚኮንዳክተሮችኤሌክትሮኒክ ክፍሎች እንዲያንሱ፣ እንዲፈጥኑ እና በኤኔርጂ ይበልጥ ብቁእ እንዲሆኑም ያስችላሉ፡፡ በሴሚኮንዳክተር ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሠሩ ኬሚስቶች የተዳማሪዎችን ጥራት ለመቆጣጠር፣ ለማሻሻል፣ እክሎችን ለማስወገድ እና በማይክሮኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ውስጥ ፈጠራ ለማምጣት ይረዳሉ፡፡ የ‹የ›-ዓይነት ሴሚኮንዳክተር (ኤሌክትሮኖች ያጠሩት) የ‹በ›-ዓይነት ሴሚኮንዳክተር (ኤሌክትሮኖች የተትረፈረፉበት) ሲሊኮን ቺፕስ እና ቅንጁ (ኢንቴግሬትድ) ሰርኩዊቶች በ1947 ተመራማሪዎች ጆን ባርዲን፣ ዊሊያም ሾክሌይ እና ዎልተር ብራቴይን የኤሌክትሪክን በሲሊኮን በኩል መፍሰስ በተናጠል ለመቆጣጠር እንደሚቻል አሳዩ፡፡ ከእዚያ ለስቆ የሲሊኮን ቺፕስ፣ የቅንጁ (integrated) ሰርኩዊቶች እና የማይክሮፕሮሴሰርስ መፈጠር ለዛሬዎቹ ባለ ከፍተኛ ፍጥነት እና ውጤታማ ኮምፒዩተሮች ፈር ቀዳጅ ሆነ፡፡ ሲሊኮን ቺፕስ (1961) በሲሊኮን ክርታሶች ላይ በአነባበሮዎች ውስጥ የተገነቡ ትራንዚስተሮችን፣ ሬዚስተሮችን፣ ካፓሲተሮችን እና የማስታወሻ ቺፖችን የሚያካትቱ፣ ከአዚያም ለብዛሕ-ደረጃ ኬሚካዊ ሂደት የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ በ1967 በቅንጁ (integrated) ሰርኩዊት፣ በብዙ ትራንዚስተሮች እና ሌሎች ኤሌክትሮኒክ ተገጣጣሚዎች ባሉት አናሳ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ አና በመጠቀም የመጀመሪያው በእጅ-ተያዥ ማስሊያ (calculator) ተሠራ፡፡ በ1980 ቅንጁ (integrated) ሰርኩዊቶች ለኮምፒዩተሮች ጥቅም ላይ ዋሉ፡፡

  3. ፪. የቴክኖሎጂ ችካሎች በመረጃ እና በመገናኛዎች ውስጥ ፪.3 የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ የመከታተያ እና የማሳያ ቴክኖሎጂዎች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኮምፒዩተር ማሳያ ቴክኖሎጂ ውስጥ አስደማሚ መሳሻሻሎች ተደርገዋል፡፡ ባለ ከፍተኛ ፍካት (resolution) ቀለማማ ግራፊክስ ማሳያዎች (screens) በዋናነት የተመሠረቱት በቴሌቪዥን ካቶድ ጨረር ቱቦ ላይ ነው፡፡ አማራጭ የማሳያ ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ለላፕቶፕ እና ለማስታወሻ-ደብተር (notebook) ኮምፒዩተሮች ዝርግ (flat-screen) ማሳያዎች አሏቸው፡፡ በተፈጥሯዊ (organic) ኬሚካሎች ላይ የተመሠረቱት ሊኩዊድ ክሪስታልስ ዲስፕሌይስ (LCD) የተፈጠሩት በ1969 ነበር፡፡ በማከታተል ከተሠሩት መካከልም እያንዳንዱ የምስል አላባ በገዝ-ራሱ የግል ትራንዚስተሮች የሚንቀሳቀስባቸው ባለ ስስ-ፊልም ትራንዚስተሮች ሊኩዊድ ክሪስታል ማሳያዎች ይገኛሉ፡፡ ኬሚስቶች ናቸው ሊኩዊድ ክሪስታል ቁሶችን፣ የቀለም ማንጠሪያዎችን፣ ፖሊመር ሰዳሪ አነባበሮዎችን፣ የተቀረጹ ፕላስቲክ የብርሃን ማከፋፈያ ቅጠሎችን እና ፕላዝማ የማሳያ ቴክኖሎጂን የፈለሰፉት፡፡ የመረጃዎች ማከማቻ መረጃ በኋላ ጥቅም ላይ ለመዋል እና ሙሉ-በሙሉ በቁጥጥር ሰር ለመዋል እንዲችል መመዝገብ አለበት፡፡ የመመዝገቢያ መሣሪያ ባለ ክፍተኛ ጥራት፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና በዋጋ ያልተወደደ እንዲሆን የሚያረጋግጡት ኬሚካዊ ፈጠራዎች ናቸው፡፡ በምዝገባ ብቃቶች (በከፍተኛ ፍካት፣ በቀልጣፋ ፍጥነት እና በቀለማማነት)፣ በፎቶግራፍ ፊልሞች፣ በመግነጢሳዊ የድምጽ መዝጋቢዎች እና በዲጂታዊ ምስል ውስጥ የመጡት ስር-ነቀል ለውጦች ጭምር ለመመዝገቢያ መሣሪያዎች ግስጋሴ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ አሜሪካዊው ፈልሳፊ እና የኮምፒዩተር አልሚ ሬይኖልድ ጆንሰን በኮምፒዩተር የተቀነባበሩ መረጃዎችን ለማከማቸት አንጋፋውን ዲስክ ድራይቭ በ1955 ሠራ፡፡ ከእዚያ ተከትለው በመስኩ በርካታ ግስጋሴዎች ተከናውነዋል፡- በተለይም በኮምፒዩተር ዲስኮች፣ በመግነጢሳዊ ጥብጣቦች (magnetic tapes) እና በ‹CD-ROM›ዎች (1984)፡፡ የመገናኛ ሳቴላይቶች እስከ 1960ዎች ድረስ በሰሜን አሜሪካ እና በሌሎች አህጉራት መካከል የድምጽ ተግባቦቶች እጅግ ውድ ነበሩ፡፡ በ1962 በዓለም የመጀመሪያዋ ተግባራዊ የመገናኛዎች ሳቴላይት፣ Telestar ወደ ምሕዋር ተላከች፡፡ እነዚያን ሳቴላይቶች ለማምጠቅ የሚያስፈልጉትን መዋቅራዊ ቁሶች (የብረታ-ብረት ውህዶች፣ ፕላስቲኮች እና ሌሎች የዘመኑ ቁሶች)፣ ኮምፒዩተር እና ኤሌክትሮኒክ ተገጣጣሚዎች፣ ብሎም የነዳጅ ቴክኖሎጂ ያቀረበውም ኬሚስትሪ ነበር፡፡ እስከ 1990ዎች ድረስ የመገናኛ ሳቴላይቶች ናቸው ዓለም-አቀፍ እና አገራዊ የረጅም-እርቀት ጥሪዎችን፣ ብሎም የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለማስፋፋት ዓቢይ ሚና የተጫወቱት፡፡ ዛሬም የመገናኛዎች ሳቴላይቶች ዲጂታዊ ቴሌቪዥን ወዳላቸው የአገር ውስጥ ሳቴላይት ዲሾች ቀጥታ ማስተላለፍን ጨምሮ በቴሌቪበዥን ስርጭቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ GPS ሳቴላይቶች በምሕዋር ላይ GPS ሳቴላይቶች ሲፈበረኩ

  4. ፪. የቴክኖሎጂ ችካሎች በመረጃ እና በመገናኛዎች ውስጥ ፪.4 የመዝናኛ ልማቶች ሲኒማዎች The Jazz Singer (የጃዝ ዘፋኙ) በ1927 ከዘፈን እና ከንግግር ጋር ተቀናጅቶ የመጀመሪያው ባለ ትረካ-እርዝመት ፊልም ሆነ፡፡ በ1930ዎች መገባደጃ ግድም ‹ቴክኒከለር› የተባለው ድርጅት ሂደቶቹን አጠራ እና የመጀመሪያው ባለ-ቀለም ተራኪ ፊልም ተሠራ፡፡ በእዚህ ጊዜ የፊልም ኬሚስትሪ መሠረታዊ ቁሶችን፣ ኬሚካዊ ወህዶችን እና ለብርሃን መጋለጥን በተመለከተ ስር-ነቀል ለውጦች አስፈለጉት፡፡ ቴሌቪዥን በ1926 ስኮትላንዳዊው ጆን ሎጊ ባይርድ በ1883 የባለቤትነት መብት ፈቃድ በተሰጠው ‹የኒፕኮቭ ዲስክ› በተባለው በሜካኒካዊ የቴሌቪዥን ሥርዓት በመጠቀም ቴሌቪዥንን ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ አሳየ፡፡ በ1927 ፊሎ ቲ. ፋርንስዎርዝ (በ1897 በተፈለሰፈው) በካቶድ ጨረር ቱቡ በመጠቀም የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን ምስል አስተላለፈ፡፡ ቀጣዮቹ ሃያ ዓመታት በኤሌክትሮኒክስ ውስጥ የወና ቱቦ (vacuum tube) ዓመታት ሲሆኑ፣ ለኤሌክትሮዶች ልዩ ቁሶች እና በቱቦው ውስጥ ለሚቆጣጠሩ አላባዎች አስተዋጽኦ ያደረገው ደግሞ ኬሚስትሪ ነበር፡፡ በ1950ዎች ውስጥ ቅንጁ (integrated) ሰርኩዊቶችን (1958) ጨምሮ በርካታ የፈጠራ ሥራዎች ተከናውነው ነበር፡፡ ተከታዮቹ አሥርት-ዓመታት ደግሞ ቅርጽ-ጠባቂ (solid-state) ምስል ማሳያ መሣሪያዎችን፣ ምስል-ማሳነሻዎችን (miniaturization) እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒካዊ መሻሻሎችን አመጡ፡፡ የኒፕኮቭ ዲስክ እና ፈጣሪው ፓል ኒፕኮቭ የባለቤትነት መብት ፈቃድ በተሰጠበት ዓመት ሥነ-ፎቶግራፍ የሥነ-ፎቶግራፍ እና የፊልም ቴክኖሎጂ ነው በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥሙንን እጅግ ጠቃሚ ተሞክሮዎች እና ሰዎች ለመመዝገብ የሚያስችለን፡፡ ኬሚስትሪ መሠረታዊ ቁሶችን፣ የተለያዩ ኬሚካዊ ውሁዶችን እና ለብርሃን መጋለጥን በተመለከተ ስር-ነቀል ለውጦችን በማምጣት ለሁሉም ዓይነት ካሜራዎች የሚያስፈልገውን ፊልም ሠራ፡፡ ውስጠ-ተከል ብልጬ ‘flash‘ ላላቸው ትናንሽ ካሜራዎች የተሠሩትን የ1950ዎችን አልካላይን-ማንጋኔዝ ባትሪዎች ጨምሮ የባትሪ መሻሻሎችም ለካሜራ ተፈላጊነት አስተዋጽኦ አደረጉ፡፡ የፊልም፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የባትሪዎች መሻሻል ደግሞ እስከ 1970 ድረስ ከ50-ሚሊዮን በላይ ወደተሸጡት የፊልም ቀፎ ወዳላቸው የ1963 የኢስትማንኮዳክ ዘነኛ ኢንስታማቲክ ካሜራዎች መፈብረክ አመራ፡፡

  5. ፪. የቴክኖሎጂ ችካሎች በመረጃ እና በመገናኛዎች ውስጥ ፪.5 የኤሌክትሮኒክስ ፈጠራዎች የተጠቃሚ ኤሌክቶሮኒክሶች እድገት የኤሌክትሮኒክ ቁሶች እና የማይክሮኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ሲዲ ማጫዎቻዎችን፣ ቴሌቪዥኖችን፣ ኮምፒዩተሮችን፣ ዲጂታዊ ካሜራዎችን እና ሽቦ-አልባ መሣሪያዎችን ለመሳሰሉ ተቆጥረው ለማያልቁ ዘመናዊ ምርቶች የደም-ስር ናቸው፡፡ ኬሚካዊ መሐንዲሶች ከወና ቱቦዎች (vacuum tubes) እስከ ትራንዚስተሮች እና ቅንጁ (integrated) ሰርኩዊቶች ድረስ ኤሌክትሮኒክሶችን ለማሳነስ፣ ይበልጥ ኃያል ለማድረግ እና በዋጋ ለማርከስ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ አዳዲስ ቁሶች፣ በከፍተኛ ደረጃ የጠሩ ቁሶችን የማምረት ሂደቶች እና ሴሚኮንዳክተሮችን የመገንባት ሂደቶች ናቸው ዓይነቶቻቸው ለተለያዩ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች አዳዲስ ብቃቶች ለመስጠት ውስብስብ ኤሌክትሮኒክ ሰርኩዊቶች ለመገጣጠም ተራንዚስተሮችን እና ቅንጁ (integrated) ሰርኩዊቶችን የመሳሰሉ ተገጣጣሚዎች ለመሥራት ያስቻሉት፡፡ የዘመኑ ረጋ-ሠራሽ (synthetic)ቁሶች የተጠቃሚ ኤለተክተትሮኒኮች፣ ተንቀሳቃሽ (cellular)ስልኮች እና የግል ኮምፒዩተሮች ስሱ ኤሌክትሮኒክ ተገጣጣሚዎችንለመታደግ የተመሠረቱት በጠንካራ፣ በዘላቂ እና በኢ-አስተላላፊ (non-conducting) ፕላስቲኮች ላይ ነው፡፡ ፕላስቲኮች ኤሌክትሪካዊ ቃንቄዎች (currents) ወደ ፕላስቲክ ሞሊኩላር መዋቅሮች ዘልቀው እናዳይገቡ የኤሌክትሮኖችን ፍሰት በሚከላከሉ የአልባሽነት (insulating) ንብረቶቻቸው ምክንያት በኤሌክትሮኒኮች አተገባበር ውስጥ ወሣኝ ናቸው፡፡ ኬሚስቶች እና መሐንዲሶች የሞሊኩሎችን መዋቅሮች በመቆጣጠር እና አዳዲሶችንም በመፍጠር ጠንካራ እና ተለማጭ (flexible) የሆኑ አዳዲስ ቁሱች ያመርታሉ፡፡ እነዚህ የመስኩ ግስጋሴዎች የግጭት መቋቋምን ለማሻሻል፣ ብሎም የመሣሪያዎችን ድምር ክብደት እና የሸማች ዕቃዎችን ዋጋ ለመቀነስ ያስቻሉ ናቸው፡፡ ትራንዚስተሮች የኮምፒዩተሮችን እና የመገናኛዎችን ጋብቻ ከማንኛቸውም ሌላ ነጠላ ልማት ይበልጥ ያስፈጸመው ትራንዚስተር የተባለው አናሳ፣ አስተማማኝ ኤሌክትሮኒክ ተገጣሚ ነበር፡፡ ጆን ባርዲን፣ ዎልተር ብራታን እና ዊሊያም ሾክሌይ በ1947 የፈለሰፉት ትራንዚስተር ምልክቶችን ለማጉላት እና ለማብራት ጥቅም ላይ ሲውሉ የቆዩትን ግዝፍ እና ተሰባሪ ወና ቱቦዎች (vacuum tubes) ደረጃ-በደረጃ ተካ፡፡ ትራንዚስተር እና እርሱን የተከተሉት (ሚሊዮናት ትራንዚስተሮች የያዙት) ቅንጁ (integrated) ሰርኩዊቶች ለዘመናዊ ኤሌክትሮኒኮች ልማት መሠረት ለመጣል ያገለገሉ ናቸው፡፡ በ1954 በሰፊው የተሰራጨው ተራንዚስተር ራዲዮ ሲቀርብ፣ በ1958 ደግሞ አሜሪካዊው የኤሌክትሪክ መሐንዲስ ሴይሙር ክሬይ ባለ ትራንዚስተር ኮምፒዩተር ሠርቶ አቀረበ፡፡ የትራንሲስተር ፈልሳፊዎች

More Related