1 / 2

የቴክኖሎጂ ችካሎች በኬሚስቱ እይታ ፫ . ጤና እና መድሐኒት

የቴክኖሎጂ ችካሎች በኬሚስቱ እይታ ፫ . ጤና እና መድሐኒት. ኬሚስትሪ ረጅም ዕድሜ እንድንኖር፣ እንድንደሰት እና ጤነኞች እንድንሆን ለማስቻል በጤና መስክ ውስጥ ለብዙ ሕይወት-አዳኝ ስር-ነቀል ለውጦች አስተዋጽኦ አድር ጓል፡፡ በአብዛኛው የሰው-ልጅ ታሪክ ውስጥ መድሐኒት እና የጤንነት ክብካቤ ኋላ-ቀር ነበሩ፡፡ ሰዎች ሲታመሙ ወይም ሲቆስሉ ሐኪሞች የሚያደርጉት ሥራ እነርሱን ከማጽናናት እና ከማጽዳት እምብዛም ያልበለጠ ነበር፡፡

Download Presentation

የቴክኖሎጂ ችካሎች በኬሚስቱ እይታ ፫ . ጤና እና መድሐኒት

An Image/Link below is provided (as is) to download presentation Download Policy: Content on the Website is provided to you AS IS for your information and personal use and may not be sold / licensed / shared on other websites without getting consent from its author. Content is provided to you AS IS for your information and personal use only. Download presentation by click this link. While downloading, if for some reason you are not able to download a presentation, the publisher may have deleted the file from their server. During download, if you can't get a presentation, the file might be deleted by the publisher.

E N D

Presentation Transcript


  1. የቴክኖሎጂ ችካሎች በኬሚስቱ እይታ ፫. ጤና እና መድሐኒት ኬሚስትሪ ረጅም ዕድሜ እንድንኖር፣ እንድንደሰት እና ጤነኞች እንድንሆን ለማስቻል በጤና መስክ ውስጥ ለብዙ ሕይወት-አዳኝ ስር-ነቀል ለውጦች አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በአብዛኛው የሰው-ልጅ ታሪክ ውስጥ መድሐኒት እና የጤንነት ክብካቤ ኋላ-ቀር ነበሩ፡፡ ሰዎች ሲታመሙ ወይም ሲቆስሉ ሐኪሞች የሚያደርጉት ሥራ እነርሱን ከማጽናናት እና ከማጽዳት እምብዛም ያልበለጠ ነበር፡፡ ሐኪሞች በሽታዎችን በመፈወስ፣ ጉዳቶችን በማስተካከል እና እንዲያውም የጤና ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት በመከላከል ረገድ ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ ስር-ነቀል ለውጦች አምጥተዋል፡፡ ትጉህ ኬሚስቶች እና ኬሚካዊ መሐንዲሶች ድንቅ መድሐኒቶችን በመሥራት፣ አዳዲስ የሕክምና መሣሪያዎችን በመፍጠር እና የበሽታ አመራመር ዘዴዎችን በማጥራት ዘመናዊ መድሐኒቶችን ለማስገኘት ረድተዋል፡፡ ሚሊዮናት የሰው-ልጅ ሕይወቶች የተረፉት እና የተሻሻሉት በኬሚስትሪ አማካኝነት በለሙ የጤና እና የሕክምና ግስጋሴዎች ነው፡፡ ፫.1 የሕመም እና የብግነት (inflammation) አያያዝ ሞርፋይን አስፒሪን ኮርቲዞን ፫.2 ሣይኮቴራፒዩቲክኤጀንቶች ክሎርፕሮማዚን ትሪሳይክሊክ አንቲዲፕሬሳንትስ ቤንዞዲያዜፒንስ ፫.3 ነቅአ-ዘሮች (hormones) እና የነቅአ-ዘር ተቆጣጣሪዎች (hormone regulators) ኢንሱሊን ቴስቶስቴሮን ፕሮጄስቲንስ፣ ኤስትሮጂንስ እና በአፍ የሚወሰዱ የወሊድ መከላከያዎች (oral contraceptives) ፫.4 ጋስትሮ-ኢንቴስቲናል ኤጀንቶች የአልሰር ሕክምና እድገት ፫.5 ሕክምናዊ ፍተሻ እና የበሽታ ምርመራ የሕክምና ምስል ማሳያ ቴክኖሎጂዎች የሕክምና አይሶቶፖች የኬሚካል መፈተሸዎች (assays) መልማት የግል ክትትል (personal monitoring) እድገት ፫.6 ፀረ-አስተላለፊ መድሐኒቶች (anti-infective drugs) ሣልቫርሣን እና ፕሮንቶሲል ፔኒሲሊን ዚዶቩዳይን (AZT) ፫.7 የካርዶቫስኩላር አያያዝ የልብ ምትን መቆጣጠር የልብን ሥራ ማቆም ማከም የደም መቋጠርን መግታት የደም ኮሌስትሮል ደረጃን መቆጣጠር ፫.8 የካንሰር ኬሚካዊ ሕክምና (chemotherapy) የካንሰር ኬሚካዊ ሕክምና እድገት ሲቶቶክሲክ መድሐኒቶች ታሞክሲፌን ፫.9 ድንቅ የጤንነት መንከባከቢያ ቁሶች ሰው-ሠራሽ ቅልጥሞች እና ሕክምናዊ መሣሪያዎች ሕክምናዊ መሣሪያዎች ፀረ-ተባያት (disinfectants) እና አንጪዎች (bleaches)

  2. ፫. የቴክኖሎጂ ችካሎች በጤና እና በሕክምና ውስጥ እለታተ-ግኝቶች 1899 ሕመምን፣ የመገጣጠሚያ ብግነትን እና እብጠትን ለመዋጋት አስፒሪን ተፈበረከ፡፡ 1909 ሣልቫርሣን የተባለው የመጀመሪያው ዋና ኬሚካዊ መድሐኒት ተሠራ፡፡ 1922 ከስኳር-በሽታ ጋር የተዛመደውን ክፍተኛ የደም ግፊት ለመቀነስ ኢንሱሊን ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ 1923 የሞርፊን ኬሚካዊ መዋቅር ታወቀ፡፡ 1927ኤስትሮጂንን በሽንት ውስጥ ለማግኘት የእርግዝና ምርመራ ተፈጠረ፡፡ 1935ፕሮንቶሲል ገዳዩን የስትሬፕቶኮካል ብግነት ፈወሰ፡፡ 1942 የናይትሮጂን ሰናፍጭ የካንሰር ኬሚካዊ ሕክምናን ዘመን ከፈተ፡፡ 1943ፔኒሲሊን ብግነትን ተዋጋ እና የፀረ-ሰውነት (antibiotic) ሕክምናን አበሰረ፡፡ 1954ዲጎክሲን የደም መቋጠርን፣ ትሮምቦቲክ በሽታን ለማከም ተረጋገጠ፡፡ 1954ክሎርፕሮማዚን ዘመናዊውን ፀረ-ሣይኮቲክ ሕክምና አስጀመረ፡፡ 1960ኤኖቪድ ተመረተ እና ለአፍአዊ የወሊድ መቆጣጠሪያነት ለገበያ ወጣ፡፡ 1963 ቅጠላ-ቅጠላዊ የሕዋስ ክፍፍል ተከላካይ (herbal cytotoxic) መድሐኒቶች ካንሰርን ለመዋጋት ጥቅም ላይ ዋሉ፡፡ 1976 የጨጓራ ቄስለቶች (ulcers) ሲታከሙ ሆድ‘ቃ ውስጥ የአሲድ ርጭትን ለመግታት ታጋሜት ተሠራ፡፡ 1977ቴሞክሲፌን በካንሰር ኬሚካዊ ሕክምና ውስጥ የነቅአ-ዘር (hormone) ገቺዎችን አስተዋወቀ፡፡ 1987ዚዶቩዳይን (AZT) ለኤች.አይ.ቪ. በሽታ ሕክምና እንዲውል የአሜሪካ ፌዴራል የመድሐኒቶች አስተዳደር ፈቃድ ሰጠ፡፡ አስፒሪን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈበረኩት እንክብሎች (1900) ፖል ኤኸሪሽ፣ የሣልቫርሣን ፈልሳፊ ኢንሱሊንን ለመጀመሪያ ጊዜ የሠሩት ፍሬዴሪክ ባንቲንግ እና ቻርልሰ ኤች. ቤስት የሞርፊን ኬሚካዊ መዋቅር የእርግዝና ፍተሸ ፐሮንቶሲል የፔኒሲሊን እንቅስቃሴ አሌክሣንደር ፍሌሚንግ በመስታወት መስኮት ላይ ሆኖ የተሠራው ሥዕል የሕዋስ ክፍፍል ተከላካዩ መድሐኒት፣ የታክሶል ኬሚካዊ መዋቅር ኤኒቪድ ሐምራዊው ጥብጣብ ለፀረ-ጡት-ካነሰር፣ ቀዩ ጥብጣብ ደግሞ ለፀረ-ኤይድስ ዘመቻ ተምሣሌቶች ናቸው፡፡ የሆድ‘ቃ ቁስለት

More Related