330 likes | 568 Views
ከኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የሚደረግ የስራ ፍልሠትና የሠዎች ዝውውር የዳሠሣ ጥናት. ዘሪሁን መሐመድ አስናቀ ከፋለ በCSSP Learn-and-Share and Relationship Building Workshop ላይ የቀረበ ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ አዳ ማ / አዲስ አበባ ጥር ፣ 2006. መግቢያ የፍልሠት አጠቃላይ ምልከታ (Overview) የስራ ፍልሠት/ስምሪት በኢትዮጵያ 3.1 የስራ ፍልሠት ወደ ደቡብ አፍሪካ
E N D
ከኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የሚደረግ የስራ ፍልሠትና የሠዎች ዝውውር የዳሠሣ ጥናት ዘሪሁንመሐመድ አስናቀከፋለ በCSSPLearn-and-Share and Relationship Building Workshop ላይ የቀረበ ፎረምፎርሶሻልስተዲስ አዳማ/አዲስአበባ ጥር፣ 2006
መግቢያ • የፍልሠት አጠቃላይ ምልከታ (Overview) • የስራ ፍልሠት/ስምሪት በኢትዮጵያ 3.1 የስራ ፍልሠት ወደ ደቡብ አፍሪካ 3.1.1 የፍልሠት መንገዶች 3.1.2 እነማን ይፈልሳሉ? 3.1.3 የፍልሠት ምክንያቶች (Push and Pull factors) 3.2. የስራ ፍልሠትና ህገ-ወጥ ዝውውር ወደ መካከለኛው ምስራቅ 3.2.1 የመ/ም የሥራ ፍልሰት ምክንያቶች 3.2.2 “ህጋዊ” እና ህገወጥ የሥራ ፍልሰት መንገዶች 3.2.3 የመ/ም የሥራ ፍልሠት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ገጽታዎች • የመንግሥት ዕርምጃዎች • መደምደሚያና የወደፊት አቅጣጫዎች • የቅርብጊዜሁነታዎች (Recent Development)
መግቢያ • የጥናቱመነሻ፡- • ሕገ-ወጥየሠዎችዝውውርአገር-አቀፍችግርመሆኑ፤ • የችግሩመስፋፋትናአሳሳቢደረጃመድረስ፤ • የግለሠቦችንሠብዓዊመብትየሚገስናየአገሪቱንገጽታየሚያጎድፍመሆኑ፤ • የችግሩንጎጂጎንበመቀነስየውጭየሥራስምሪትለልማትየሚውልበትንመንገድመሻትአስፈላጊበመሆኑ፡፡ • የጥናቱዓላማ፡- • ወደ መ/ም እና ደ/አ የሚደረጉየስራፍልሠትናየሠዎችዝውውርባህሪያትንለመረዳት፤ • የስራስምሪትአስተዳደር፣ ፖሊሲዎችናመዋቅሮችንመተንተንናክፍተታቸውንመረዳት፤ • ችግሩየሚቃለልበትንየፖሊሲኃሳቦችማመንጨት፤ • የጥናቱዘዴ፡- • በተመረጡክልሎች፣ ወረዳዎችናአካባቢዎችመረጃዎችበማሠባሠብ፤ • ኦፊሴላዊመረጃዎችንበማሰባሰብናበመተንተን(ሠ/ማ/ጉ/ሚ፣ UNHCR, IOM) • ሌሎችየታተሙናያልታተሙጽሁፎችበማጣቀስ፤ • በአመዛኙ ኢ-አኃዛዊመረጃ (Qualitative data) ላይየተመሠረተጥናትነው፡፡
የፍልሠትአጠቃላይምልከታ (Overview) • ፍልሠትበተለያየዩምክንያቶችያሉበትንአካባቢትቶወደሌላአካባቢየሚደረግጉዞናኑሮሊባልይችላል፡፡ • የተለያዩየፍልሠትዓይነቶችአሉ፡- በጊዜ(የአጭርናየረጅም)፣ በቦታ(የአገርውስጥናየውጭ)፣ በአካባቢ(የከተማናየገጠር) ይከፋፈላሉ፡፡ • ፍልሠትጥንታዊሁነትሲሆንዓለምዛሬለምትገኝበትየፖለቲካ፣ ማኀበራዊናኢኮኖሚያዊሁኔታጉልህአስተዋጽዖአበርክቷል፡፡ ለምሳሌ በ2009 የዓለምየፍልሠትመጠን 3% የደረሠሲሆንከዚህውስጥየአፍሪካድርሻ 1.9% ነበር (UNDP)፡፡ • ፍልሠትአዎንታዊምአሉታዊምገጽታዎችአሉት፡፡ • በአዎንታዊጎኑ፤- የስራ፣ የትምህርት፣ የልምድልውውጥ፣ የህዝቦችመቀራረብ፣ የአገራትየገቢምንጭ፣ የቴክኖሎጂዝውውር … • በአሉታዊጎኑ፤- የተማረየሠውኃይልመመናመን፣ የሠብዓዊመብትጥሠት፣ የህገ-ወጥአዘዋዋሪዎችመበራከት፣ በፈላሲናተቀባይህዝቦችመካከልየሚከሠቱግጭቶች፣ ጭፍንጥላቻ (Xenophobia) …
የቀጠለ … • በኢትዮጵያ ፍልሠት ረጅም ታሪክ አለው፡፡ የቅርቡን ብንመለከት በ3 ዋና ዋና ክፍለ-ጊዜያት ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡ ሀ. ቅድመ 1966 አብዮት ዘመን፡- • በመጠን ውስን፣ ተምሮ ወደ አገር መመለስ፣ • የስራ ፍልሠት እጅግ ውስን የነበረበት ወቅት ለ. 1966 – 1983፡- • የፖለቲካ ስደት ያየለበት • በአብዛኛው ወደ ምዕራቡ ዓለም፡፡ የስራ ፍልሠት ወደ መ/ም ጅማሮ፡፡ • ነገር ግን የመዘዋወር መብትን የገደበ ፍልሠትን በአሉታዊነት የሚመለከት ፖሊሲ፡፡ ሐ. ድህረ- 1983፡- • የመንቀሳቀስ መብት መከበር፤ • ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስደት እና ከፍተኛ የስራ ፍልሰት የታየበት ወቅት ነው፡፡
የስራፍልሠት/ስምሪትበኢትዮጵያ • የስራ ፍልሠት (Labour Migration):- • ሠፊ የስራ ፍልሠት በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ አለው ለማለት አያስደፍርም፡፡ • በመ/ም (በተለይ ወደ ሳዑዲ አረቢያ) በ1970ዎቹ መጀመሪያ ከሀጅና ዑምራ ፀሎት ጋር ተያይዞ በጥቂት ደረጃ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ • ለፀሎት የሚሄደው ሠው ኮታ ውስን መሆን፣ የቪዛ አሰጣጥ ቁጥጥር፣ ሴቶች ብቻቸውን እንዳይሄዱ የሚያዘው ኃይማኖታዊ ህግና የሚያስከትለው ከፍተኛ ወጪ፣ ለፍልሠት ቀና አመለካከት የሌለው ፖሊሲ መጠኑን ገድበውታል፡፡ • በአሁኑ ጊዜ የስራ ፍልሠት (በተለይ ወደ መ/ም) እጅግ ተስፋፍቶ ይገኛል፡፡ ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፡፡ • ውስጣዊ ምክንያት፡- የመንቀሳቀስና መሠረታዊ የማንነት ሠነዶችን (ለምሳሌ. ፓስፖርት፣ የልደት ሠርተፊኬት) የማግኘት መብት መከበር፤ • ውጫዊ ምክንያት፡- በገልፍ አገሮች የመጣው ፈጣን የኢኮኖሚ ብልፅግና፤ የኑሮ ደረጃ ዕድገትና የሠው ኃይል ፍላጎት፡፡ • ዛሬ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን (በአብዛኛው የቤት ሠራተኛ ሴቶች) በመ/ም አገሮች ይገኛሉ፡፡ • በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረግ ፍልሰት እ.ኤ.አ ከ1990ዎቹ ወዲህ ተስፋፍቶ ይገኛል፡፡
3.1 የስራፍልሠትወደደቡብአፍሪካ • ምንም እንኳን ጥቂት ኢትዮጵያውያን እ.ኤ.አ. ከ1991 በፊት በደ/አ የነበሩ ቢሆኑም በገፍ መጓዝ የተጀመረው ከእ.ኤ.አ 1995 በኋላ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለዚህም በአገር ውስጥና በደ/አ የደረሱ ለውጦች ምክንያት ናቸው፡፡ • በአገር ውስጥ፡- • የ1883 ዓ.ም. ለውጥና የመንቀሳቀስና መሠረታዊ የግል ሠነዶች ካለቅድመሁኔታ የማግኘት መብቶች መጠበቅ • የ1983ዓ.ም ለውጥን ተከትሎ ብዛት ያለው ስደተኛ ወደ ኬንያ መግባቱና የተወሰኑት ወደ ደ/አ መድረስና መኖር መጀመር፤ • በደ/አፍሪካ፡- • የዘር መድልዎ ስርዓት መውደቅና ተያይዞ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ናቸው፡፡ • በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ያለው የቪዛ ስምምነት (Visa Weiver) ወደ ደ/ለመጓዝ ምቹ መሸጋገሪያ ሆኗል፡፡ • በአሁኑ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ብዙ አስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች/ፈላሲያን አሉ ተብሎ ይገመታል፡፡
3.1.1 የፍልሠትመንገዶች • ወደደ/አ የሚደረገው ፍልሠት በአመዛኙ ህገ-ወጥ ሲሆን ጥቂቶች በተለያዩ “ህጋዊ” መንገዶች ይጓዛሉ (ጉብኝት፣ ንግድ፣ ህክምና …)፡፡ በዚህም ብዛት ያላቸው ዜጎች ደ/አ ይገኛሉ፡፡ • ለምሳሌ፡ በእ.ኤ.አ በደ/አ 2011 የቢዝነስ ፍቃድ ከተሠጣቸው 1364 ሠዎች መካከል 8.2% (110፣ 4ኛ) የስደተኛነት ፍቃድ ካገኙት ደግሞ 1% (17፣ 6ኛ) ያህሉ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡
የቀጠለ … • ወደ ደ/አ የሚደረግ ፍልሠት በቅርቡ እጅግ በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በሀዲያ ዞን ግቤ ወረዳ ያለውን ቁንጽል ቁጥር ብናይ፤
የቀጠለ … • ወደ ደ/አ የሚደረገው ህገ-ወጥ ፍልሠት በሁለት አይነት ይካሄዳል - በየብስ እና በአየር • በየብስ (እግር)፡- ኢትዮጵያ →ኬንያ → ታንዛንያ → ማላዊ/ሞዛምቢክ/ → ዝምባቡዌ →ደ. አ • በአየር ጉዞ ፡- ቀጥታ ጉዞ ወይንም ወደ ጎረቤት አገር (ቀጥሎ በእግር ድንበር በማሳበር → ደ/አ) • ደ/አ ከደረሱ በኋላ ብዙዎቹ በDep. of Home Office በስደተኝነት በመመዝገብ ይኖራሉ፡፡ በአብዛኛው በእምነት ላይ የተመሠረተ አነስተኛ ንግድ ስራ ላይ በመሠማራት ኑሯቸውን ይገፋሉ፡፡ • ማኀበራዊ ትስስር (social network) የስደት መነሻና በደ/አ ለመኖርና ለመስራት ያገለግላል (ቀድሞ የሄደ የቤተሠብ አባል፣ ጎሳ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ ያገር ልጅ …) • በደ/አ ፈላሲዎቹ ሁለት አይነት ማንነት ይኖራቸዋል- የኢኮኖሚ ፈላሲ እና የፖለቲካ ስደተኛ (economic migrants Vs polical refugees).
3.1.2 እነማንይፈልሳሉ? በፆታ ረገድ ወንድ ብቻ! በሀዲያ ዞን ግቤ ወረዳ ወንድ 925 ሴት 1 ሴቶች በትዳር (new trend) በትምህርት ደረጃና የስራ ሁኔታ ከስራ አጥ --- BA/BSc ደረጃ ሁ/ደ/ት/ ያጠናቀቁና ያቋረጡ ወጣቶች የግብርና ባለሞያ (ኤክስቴንሽን) መምህር፣ ፖሊስ፤ Other civil servants
በዕድሜ፡- 15- 60 አመት በአመዛኙ 18-35 ዓመት ያለ ወጣት በአካባቢ፡- በተወሠነ ደረጃ ከሁሉም የአገሪቱ ክፍል በተለይ የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል፤ ከምባታ ዞን ሀዲያ ዞን ጠንባሮ ወረዳ ሀላባ ልዩ ወረዳ ወላይታ ዞን አጎራባች ክልል፣ ዞንና ወረዳዎች ለምን? ምናልባት ቀደም ብለው የሄዱ ሰዎች ምሳሌ፤ የአካባቢዎቹ የፍልሠት ታሪክ፤
3. 1.3 የፍልሠትምክንያቶች (Push and Pull factors) • ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የፍልሰቱ ዋና ምክንያት ነው፡- ሠርቶ ገንዘብ ማግኘት! • Push factors: • ስራ አጥነት (በተለይ የወጣት ስራ አጥነት)፡- ለምሳሌ፤ በ2003 በደ/ብ/ብ/ህ/ክ የተመረጡ ዞኖችና ወረዳዎች የተደረገ የስራ አጥነት ዳሠሣ ጥናት ወጣቶች ከፍተኛ የስራ አጥነት ችግር እንዳለባቸው ያሳያል፡፡ (19-24 ዕድሜ =53.23% ከ14-35 =86.7%) • “ድህነት” ፡- “ብሠራ ብሠራ ጠብ አልልም አለኝ!“ ነገር ግን ለጉዞ በአማካይ እስከ 32,000 ብር ይከፈላል፡፡ (ከፍተኛው ብር 140,000 ዝቅተኛው 5,000) • በአቋራጭ የመክበር ፍላጎት፡- አንዳንድ የተሳካላቸውን ተመላሾች በማየት አገር ውስጥ ሠርቶ የመኖር ፍላጎት ማጣት፤ • ቤተሠብ፣ የጓደኛ፣ የአካባቢ ግፊት፡- አንዳንድ የሀይማኖት አባቶችና የአካባቢ ሽማግሌዎች ሳይቀሩ በዚህ ይወቀሳሉ፡፡
የቀጠለ… • Pull factors: • በደ/አ ሠርቶ የማግኘት ዕድል: • የደ/አ መንግስት የስደተኞች ፖሊሲ (የስራ ፈላሲ የመቀበል የረጂም ጊዜ ታሪክና tolerance) • ሌሎች ምክንያቶች፡ • ህገ-ወጥ ደላሎች- በአገር ውስጥና በውጭ አገራት (ኬኒያ፣ ታንዛኒያ፣ ሞዛምቢክ፣ ዙምባብዌ ….) • ጠንካራ network አላቸው፡፡
3.2. የስራፍልሠትናህገ-ወጥዝውውርወደመካከለኛውምስራቅ • ወደ መ/ም የኢትዮጵያውያን ለሥራ መሄድ የተጀመረው በ1970ዎቹ ቢሆንም በቁጥር በርካታ ኢትዮጵያውያን መሄድ የጀመሩት ከ1983 በኋላ ነው፡፡ • እ.ኤ.አ በ1983 ሠ/ማ/ጉ/ሚ ለ1355 ሰዎች የሥራ ፈቃድ ሲሰጥ፤ከዚህ ውስጥ 43% ሴቶች ነበሩ፡፡ • እ.ኤ.አ 2001 ሠ/ማ/ጉ/ሚ 5015 ፈቃድ ሲሰጥ ከእነዚህ ውስጥ 98% ሴቶች ነበሩ:: • እ.ኤ.አ 2004-2006፤ 57084 ሠራተኞች ሲሄዱ ከእነዚህ ውስጥ 98.6% ሴቶች ነበሩ:: • ሳውዲ አረቢያ በ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያን የቤት ሠራተኞች ማስገባት ከመጀመሩዋ በፊት አብዛኛዎቹ ፈላሲዎች ይሄዱ የነበረው ወደ ሊባኖስ ነበር፡፡
የቀጠለ … • ምንም እንኩዋን ወደ መ/ም የሚሄዱ ሠራተኞች ብዙ እንግልትና ስቃይ ቢደርሰባቸውም በርካታ ሰዎች በህጋዊና ህገወጥ በሆነ መንግድ ለሥራ መሄዳቸው አልቀረም፡፡ • ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ኢትዮጵያውያን (ከአብዛኛው የአገሪትዋ ክፍሎች) ወደ መ/ም በመፍለስ ላይ ናቸው፡፡ • በተመሳሳይ ሁኔታ አያሌ ኢትዮጵያውያን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር በመሻገር ወደ መ/ም ይጓዛሉ፡፡ • ፈላሲዎቹ ወደ ተለያዩ አገራት ቢሄዱም ሳዑዲ አረቢያ ዋና ተቀባይ አገር ሆና ትገኛለች፡፡
3.2.1 Factors for Migration to the ME • Pull factors: • Job opportunities • Improving livelihoods, asset building • The support of family members and other Ethiopians in the ME • Push factors: • Limitation/lack of job opportunities (particularly limitation of non-farming opportunities for rural women); • Peer and family pressure; • Eagerness for new experience; • Impact of some ‘successful” returnees (e.g. Dubai village in Eteya, Oromia; newly build houses in Robit, AmbasselWollo) • However, significant number of people with stable jobs also migrate (e.g. teachers, police officers, health extension workers)
3.2.2 “ህጋዊ” እና ህገወጥ የሥራ ፍልሰት መንገዶች • የህጋዊ እና ህገወጥ የስራ ፍልሰት ጉዳይ በመስኩ በከፍተኛ ደረጃ አነጋጋሪ ሆኖ ይታያል፡፡ • ህጋዊው የሥራ ፍልሰት በቅጥር አጄንሲዎች አማካይነት በሠ/ማ/ጉ/ሚ ፈቃጅነት መንግስት ያወጣቸውን መስፈርቶችና ግዴታዎች በሟሟላት የሚከናወን የሥራ ስምሪት ሂደት ነው፡፡ • በአሁኑ ወቅት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በዚህ መስመር ወደ መ/ም ይሄዳሉ፡፡ በተለይ የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያውንን በገፍ ለቤት ውስጥ ሥራ ማስገባት ከጀመረ ወዲህ በዚህ መስመር ወደ መ/ም የሚሄዱ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ • ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት ከኩዌትና ከተባበሩት አረብ ኤሚሬት ጋር ሲኖራት፤ ከተ.አ.ኤሚሬት ጋር የተደረገው ስምምነት ሥራ ላይ አልዋለም፡፡ • ከሳዑዲ አረቢያ ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በመንግስታቱ መካከል እስከሁን አልተደረሠም፡፡ አሁን የሚደረገው የስራ ፍልሠት የሚከናወነው በ2ቱ አገሮች የቀጣሪ ኤጄንሲ ማኀበራት ስምምነት ነው፡፡
የቀጠለ … • የሁለትዮሽ የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነት ጥሩ እርምጃ ቢሆንም፤ በህጋዊ መንገድ የሚሄዱ ሠራቶኞች መብት ሚሉ በሙሉ ያስከበራል ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ • ተቀጣሪ ሠረተኞች ወደተቀባይ አገራት የሚሄዱትና የሚኖሩት በአሰሪው መልካም ፈቃድ ላይ በተመሠረተው (sponsorship) በሚባለው ማዕቀፍ ነው፡፡ • ኤጅንሲዎች ህጋዊውና ህገወጡን ቀላቅለው ይሰራሉ የሚል ከፍ ያለ ጥርጣሬ አለ፡፡ • ህገ ወጥ የሥራ ፍልሰት በቦሌና በባህር የሚደረግ ሲሆን በባህር በአብዛኛው የሚሄዱት ወንዶች ናቸው፡፡
የቀጠለ … • በብዙ አጥኝዎች ግምትና የዓለም የስደተኞች ድርጅት የመን በባህር ስለሚደደርሱ ስደተኞች የሚያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፡ ህገወጥ ፍልሰት ከህጋዊው ይበልጣል ተብሎ ይገመታል፡፡ • ለህገወጡ ፍልሰት መስፋፋት ዋና ዋና ምክንያቶች • በተቀባይ አገሮች በህጋዊውና በህገወጡ መሃከል ያለው ልዩነት መደብዘዝ፤ እንዲያውም በህገወጥ የገቡ ሰዎች ከስፖንሰርሺፕ ውጭ መንቀሳቀስ፡፡ • በአገር ውስጥ ህጋዊው መንገድ ላይ ያሉ ጫናዎች (ፓስፖርት ማውጣትና የጤና ምርመራ የሚወስዱት ጊዜ፤ የደላሎች ጫናና ወከባና ሌሎች ምክንያቶች፡፡
ህገወጥ ፍልሠትን በአካሄድ መንገዱ በመነሳት በሁለት መክፈል ይቻላል፡፡ • በህገወጥ በልዩ ልዩ መንገድ (በእግር ጭምር) በየብስ ድንበር በማቋረጥ ወደ ጎረቤት ሀገራት በመሄድ ወደ መ/ም መግባት (ጅቡቲ፣ የመን፣ ሱዳን፣ ሶማሌላነድ):: • በህገወጥ መንገድ የውጭ የስራ ፎረማሊቲዎችን ሳያሟሉ በልዩ ልዩ ሠበቦች ወደ ሚፈልሱበት አገር በቀጥታ በበረራ መሄድ፡፡ (አንዳንድ የግል የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች በዚህ ረገድ ሚና አላቸው ተብሎ ይወቀሳሉ)፡፡ • ድንበር በማቋረጥ የሚወጡት ሁለቱም ጾታ ቢሆኑም የወንዶች ቁጥር እንደሚያመዝን ይነገራል፡፡ ለዚህም ለወንዶች የሚሆን ስራ በህጋዊ የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች በብዛት የማይታቀፍ መሆኑ ዋናው ምክንያት ነው፡፡
3.2.3 የመ/ም የሥራ ፍልሠት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ገጽታዎች • በአብዛኛው ወደ መ/ም የሚሄዱት ሴቶች ናቸው (feminization of migrants)፤ ወንዶች በኤጄንሲ በኩል አይሄዱም፡፡ • የሥራ ፍልሰቱ ጎጂና በጎ ኢኮኖሚያዊ ገጽታዎች አሉት፤ በእርግጥም ኑሮዋቸውን ያሻሻሉ ሲኖሩ፤ ሌሎች ደግሞ ከስራ የተፈናቀሉ፤ በአራጣ ብድር ምክንያት የደኸዩ፤ ሥነ ልቦናዊና አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው የተመለሱ በርካቶች አሉ፡፡ • የሥራ ፍልሰቱ በርካታ ማህበራዊ እንድምታዎች አሉት ለምሳሌ፤ • ሴቶች ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጭ መንቀሳቀስ፤ • ህብረተሰቡ ለሴቶች የሚሰጠው ቦታ መጨመር፤ • ሴቶች ከትምህርት በተለይ አንደኛ ደረጃን ጨርሰው ማቋረጥ፤ • ዕድሜያቸው 18 ያልሞላ ልጆች/ታዳጊ ወጣቶች ፓስፖርት በማውጣት የሥራ ፍልሰቱን መቀላቀል፡፡
የቀጠለ … • በሚላከው ገንዘብ ሳቢያ በቤተሰብና በትዳር ጓደኛ ፣ በባልና ሚስት ወ.ዘ.ተ. መካከል ግጭት መፈጠር • በእናቶች መሄድ ምክንያት በትንንሽ ሴት ልጆች ላይ የቤት ሥራ ጫና መብዛት፤ ልጆች የእናት እንክብካቤ በማጣት በትምህርት መድከምና ማቋረጥ፤ ባሎች የቤት ውስጥ ሥራ ላይ መሰማራት መጀመርና በሌሎች ስራዎች ላይ ያለው ተጽዕኖና ሌሎች ናቸው፡፡
የመንግሥት ዕርምጃ ዎች • ህጋዊ የውጭ የሥራ ሥምሪትን የሚያበረታቱ ህጎች ማውጣት (አዋጅ ቁጥር 104/1990ና 632/2001)፤ • የሠራተኛ ልውውጥ ስምምነቶች ከተቀባይ አገራት ጋር መስማማት (ኩዌትና አረብ ኤሚሬት)፤ • ምንም እንኳን የዘገየ ቢሆንም መንግሥት ህገወጥ ዝውውርን ለመቆጣጠር የሚከተሉት እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል • የሠው ዝውውርን የሚቆጣጠረው ም/ቤት ከረጅም ጊዜ በኋላ እንቅሰቃሴ መጀመርና መዋቅሩን ማስፋፋት፤ • በህገወጥ ዝውውር ላይ አገር አቀፍ ዘመቻ መጀመር፤ • ግንዛቤ የማስፋት ጥረት ማድረግ፤ • ለፈላሲ ሠራተኞች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሥልጠና መስጠት፤
የቀጠለ … • የመንግሥት ዘመቻ ግን ብዙ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል፡፡ ከነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹ፤ • በህብረተሠቡ ውስጥ የግንዛቤ ማነስና ኋላቀር አመለካከት፡- ውጭ አገር መሄድን እንደ ጥሩ ዕድልና አጋጣሚ የመመልከት ሁኔታ፤ • በአገር ውስጥ የተፈጠሩት የስራ እድሎች ውስንነት፤ የተማረ ስራ አጥ መበራከት፤ • የደላሎች ቅስቀሳና ምስጢራዊ ሰንሰለቶች፤ • የአንዳንድ ኤጅንሲዎች ህጋዊውንና ህገወጡን ስራ መቀላቀል፤ • የሠ/ማ/ጉ/ሚ አቅም ውስንነትና ከክልሎች ጋር ያለው የቅንጅት ማነስ፤ • በህጋዊና በህገወጥ መንገድ በሚወጡ የስራ ፈላሲያን መሀከል በተቀባይ አገራት ውስጥ የመብት ጥበቃና እንክብካቤ ብዙ ልዩነት አለመኖር፤ • የስራ ሥልጠናዎች ከስራ ስምሪት ጋር አለመቆራኘት፤
5. መደምደሚያና የወደፊት አቅጣጫዎች • በአገራችን ስለስራ ፍልሠት ያለው አመለካከት መቀየር ይኖርበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሁለት ጽንፍ የያዙ አመለካከቶች ይንጸባረቃሉ፡፡ ሀ. የስራ ፍልሠት እንደ “በረከት”፡- በአብዛኛው በህብረተሠቡ ውስጥ ያለ አመለካከት (folk view) ለ. የስራ ፍልሠት እንደ “መርገምት”፡-በአብዛኛው በሚዲያና፣ ማኀበራዊ ድህረ-ገጾች፣ • ነገር ግን የስራ ፍልሠት ሁለቱንም የያዘ ነው፡፡ • ትክክለኛ ፖሊሲና ስትራቴጂ ያለው፣ በዕቅድ የሚመራ፣ በሚገባ የተደራጀና የተቀናጀና የስራ ፍልሠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ለዚህም በምሳሌነት ከውጭ የሚመጣውን የውጭ ምንዛሪ መመልከት ይቻላል፡፡
ዘላቂ የውጭ የሥራ ስምሪት ፖሊሲና ስትራቴጂ ማውጣትና መተግበር፤ • ህጋዊው የተሻለ ሥልጠና፤ ጥበቃ፤ ጥቅም የሚያስገኝ እንዲሆን ማድረግ፤ • ፍጥነትና ቅልጥፍና ሠዎች በህገወጥ መንገድ መጓዝን በአማራጭነት እንዲወስዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በመሆኑም የፓስፖርተ፣ አሻራ፣ የጤና ምርመራ የመሣሠሉት አገልግሎቶች በህጋዊ መንገድ ለመጓዝ ለሚሹ ዜጎች በክልሎች በቀላሉና በተቀላጠፈ መንገድ እንዲደርሱ ማድረግ፡፡ • በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይ አገሮች የፈላሲ ሠራተኞችን መብት እንዲያክብሩ መስራት፤ • በስራ ፍልሰት ከሚታወቁ ሌሎች አገሮች ጋር ልምድ መጋራትና አብሮ መስራት፤
6. የቅርብጊዜሁነታዎች (Recent Development) • የኢትዮጵያ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ በስራ ፈላሲያን ላይ የሚደርሠውን ችግር ለማቃለል አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምሯል፡፡ • በሐምሌ 2005 GAMCA (Gulf Approved Medical Clinics’ Association) የተባለውን የምርመራ ድርጅት ሲያግድ፤ ቀጥሎም ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚደረገው ፍልሠት ላለተወሠነ ጊዜ እንዲታገድ ተደርገጓል፡፡ • በሌላ በኩል እነዚህ እርምጃዎች (በተለይ በጎረቤት አገራት በኩል የሚደረገውን ) ህገ-ወጥ ፍልሠት እጅግ አባብሶታል፡፡ • የ ሳዑዲ አረቢያ መንግስት በበኩሉ ህገ-ወጥ ባላቸውን ስደተኞች ከአገር የማስወጣት ዘመቻ በኅዳር 2006 ጀምሯል፡፡ • በእ.ኤ.አ. 2013 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ህገ-ወጥ ያላቸውን ስደተኞች እስከ ኖቬምበር 4 ቀን 2013 ድረስ ህጋዊ የመኖሪያ/የስራ ሠነድ እንዲይዙ ወይም ከአገር እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሠጠ፡፡
የተባለው ጊዜ ከመድረሱ አስቀድሞ የሳዑዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚገኙባቸው ጂዳ፤ ሪያድና መሠል ከተሞች ከበባ አድርገው ብዛት ያላቸው ስደተኞችን በማጎሪያ ስፍራ እንዳጎሯቸው ይነገራል፡፡ • በዚህ ዘመቻ በመጀመሪያ 30 ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ተብሎ ቢገመትም በ IOM መረጃ መሠረት በአሁኑ ጊዜ ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሾች ቁጥር ወደ 155 ሺ ደርሷል ፡፡ • ከተመላሾች መካከል 65% ያህሉ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪው 35% ሴት ተመላሾች ናቸው፡፡ • እንዲሁም ህጻናትና (7,915) ከቤተሠቦቻቸው የተነጠሉ ልጆችም (unaccompanied minors [421]) ይገኙባቸዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ከተመላሾች ጋር በተያያዘ አገሪቱ አዲስ ተግዳሮቶችን ተጋፍጣለች፡፡ እነዚህ ተግዳሮቶች ከሁለት አቅጣጫ የሚነሱ ይሆናሉ፡፡ • አስቸኳይ ጊዜ ተግዳሮት (Immediate challenge): ይህ ተግዳሮት ስደተኞችን ወደአገራቸው የመመለስ፣ ጊዜያዊ ማረፊያ ማዘጋጀት፣ ህክምና፣ ምግብና ልሎች ለመሳሳይ ድጋፎችን ማድረግን ያካትታል • በዘላቂነት የማቋቋም ተግዳሮት (Long-term rehabilitation): ይህ በዋናነት ተመላሾች በኑሮ ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ጥሪታቸውን ያሟጠጡ፣ ቀደም ሲል ይዘው ከነበሩት የስራ መስክ (career) የተራራቁ፣ ከሌላ ክፍል ሊያገኙ የሚችሉት ድጋፍ ውስን የሆነ በመሆኑ በቤተሠቦቻቸው ጥገኝነት ላይ የመውደቅ አደጋ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ • የስደት ተመላሎች ችግር ሁለት መልክ ያለው ነው፡- በራሳቸው በተመላሾችና በእነርሱ ሲረዱ በነበሩት ቤተሠቦቻቸውና ጥገኞቻቸው ላይ! • ችግሩ ወቅታዊ ምላሽ ካልተሠጠው አንዳንድ ተመላሾች ዳግም ለተመሳሳይ ስደት አይነሳሱም ማለት ያስቸግራል፡፡ • በመሆኑም አሁን ከተከሠተው ችግር መጠንና ስፋት አንፃር መልሶ የማቋቋሙ ፕሮግራም የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ፣ ቅንጅትና ከሁሉም በላይ ሪሶርስ የሚጠይቅ ይሆናል ተብሎ ይታመናል