1 / 4

የ ናይትሮጂን ማረጋጊያ

፬ . የቴክኖሎጂ ችካሎች በምግብ እና በእርሻ ውስጥ. ፬ .1 ማዳበሪያዎች እና አፈር አልሚዎች. የ ናይትሮጂን ማረጋጊያ

ula
Download Presentation

የ ናይትሮጂን ማረጋጊያ

An Image/Link below is provided (as is) to download presentation Download Policy: Content on the Website is provided to you AS IS for your information and personal use and may not be sold / licensed / shared on other websites without getting consent from its author. Content is provided to you AS IS for your information and personal use only. Download presentation by click this link. While downloading, if for some reason you are not able to download a presentation, the publisher may have deleted the file from their server. During download, if you can't get a presentation, the file might be deleted by the publisher.

E N D

Presentation Transcript


  1. ፬. የቴክኖሎጂ ችካሎች በምግብ እና በእርሻ ውስጥ ፬.1 ማዳበሪያዎች እና አፈር አልሚዎች የናይትሮጂን ማረጋጊያ የናይትሮጂን ማረጋጊያ ማይክሮኦርጋኒዝሞች አናሳ-አጸፋ-መላሽ ናይትሮጂንን ፣በተራቸው በቅድሚያ እንደ ሕይወታዊ ናይትሮጂን ውህዶች ወደ አልሚ-ምግብ ሰንሰለት ወደሚገቡት እጽዋት ውስጥ ያሉትን ፕሮቲኖች፣ወደ ሕይወት-አልባ (inorganic) ውህዶች የሚለውጥ አንድ አስፈላጊ ተፈጥሯዊ ሂደት ነው፡፡ የሚገኝ የአፈር ናይትሮጂን፣ በተለይም ናይትሬቶች ፣ ሰብልን በገፍ ለማምረት ለወትሮው ጉድለት አለበት፡፡ ለአሞኒያ ቅመማ በምርጥነት የታወቀውን የሃበር-ቦሽ ዘዴ ጨምሮ ናይትሮጂን ማዳበሪያዎችን አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ የተዘጋጁ በርካታ ሂደቶች አሉ፡፡ የተመጣጠነ አፈር ኬሚስትሪ ተገኝነት ጭምር በሕይወታዊ ውህዶች (organic compounds) ውስጥ ያለውን ናይትሮጂን መጠን ውዲያውኑ ለመተንተን በሚያስችለው በ1956 የኪያልዳህል ዘዴ ስርጸት እመርታ አሳየ፡፡ የናይትሮጂን ዑደት የስር እባጮች (nodules) የሃበር-ቦሽ ሂደት በ19ኛው ምእት-ዓመት መገባደጃ ላይ እየበዛ ለመጣው የዓለም ሕዝብ የነበረው ውሱን የምግብ አቅርቦት እጅጉን አሳሳቢ ሆነ፡፡ የእርሻ አፈር የናይትሮጂን ይዘት ተዳክሞ እና ለናይትሮጂን ማዳበሪያዎች የተጠየቀው የኢንዱስትሪ ድጋፍ መፍትሄ ሳያገኝ ቀርቶ ነበር፡፡ አንዳንድ ሣይንቲስቶችም ረሃብ በስፋተ-ዓለም ደረጃ እንደሚከሰት ተነበዩ፡፡ ስለእዚህ ናይትሮጂንን ከአየር ወስዶ የናይትሮጂን ውህዶችን ማምረት አንገብጋቢ ሆነ፡፡ መፍትሄው ፍሪትዝ ሃበር በውቅቱ የነበሩትን ሁሉንም አካላዊ እና ኪሚካዊ ሃብታት ተጠቅሞ የአሞኒያን ቅመማ ካገኘባት ከወደ ጀርመን በ1908 መጣ፡፡ ቅመማው የተከናወነው በከፍተኛ ግፊት እና መጠነ-ሙቀት በብረት አርሾነት (iron catalyst) ነበር፡፡ የBASF (Badische Anilin-& Soda-Fabrik) ኬሚስቱ ካርል ቦሽ አንጋፋውን እና ዘመናዊውን የኢንዱስትሪ ደረጃ ምርት በማስተዋወቅ ሂደቱን በ1913 ለንግድ ሥራ አዋለ፡፡ ይህ ኢንዱስትሪያዊ ሂደት ነበር በ20ኛው ምእት-ዓመት ውስጥ የእርሻ ምርት እና የሕዝብ ብዛት እንዲስፋፉ ያስቻለው፡፡ ፍሪትዝ ሃበር ግስጋሴዎች በኬሚካዊ ማዳበሪያዎች ውስጥ ረጋ-ሠራሽ ማዳበሪያዎች ከ1913 ጀምሮ ለገበያ መመረታቸው የሰብል ብዛት እና ምርት በእጅጉን እንዲሻሻሉ አደረገ፡፡ ከእዚያን ጊዜ ወዲህ በ1930 ለገበያ የቀረቡትን ሽርክት ማዳበሪያዎች እና በ1965 ለአሜሪካ ገበያ የወጡትን ተረጪ (suspension) ማዳበሪያዎች ጨምሮ በኬሚካዊ ማዳበሪያዎች መሠረታዊ አመራረት ውስጥ የፈጠራ-ሥራዎች ተከናወኑ፡፡ በ1970ዎች ውስጥ ለጓዳ-ሠራሽ ቅመማ አመቺ የሆኑ ማዳበሪያዎችን ለማስተዋወቅ ሽርከታ ይበልጥ እንዲጠራ ተደረገ፡፡ በቅርቡ ለገበያ ከቀረቡ የፈጠራ-ሥራዎች መካከል ለሥነ-ምሕዳር የማያስፈልግ ከልክ ያለፈ የማዳበሪያ አጠቃቀምን የሚያስቀሩ በተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚረጩ ተሸፋኝ ማዳበሪያዎች ይጠቀሳሉ፡፡ አረንጓዴ አብዮት እና ድቅል እጽዋት ድቅል እጽዋት ከ1870ዎች አንስቶ የተፈጠሩት የምግብ ምርተን እና ጥራትን ለማሳደግ በሚችሉ ተፈላጊ ባሕሪያት ለመጠቀም ተፈልጎ ነው፡፡ ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ተፈላጊ የእጽዋት ዓይነቶችን ለይቶ እነዚያን ዓይነቶች ወደ ተከታታይ ድቅሎች በመተርጎም ከኬሚካዊ ማዳበሪያዎች ጋር የናይትሮጂን አወሳሰዳቸውንከፍ ያደርጋል፡፡ እነዚህ ግስጋሴዎች ናቸው ሜክሲኮ በ1943 በስንዴ ምርት ራሷን በመቻል ረገድ የመጀመሪያዋ ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ ወደ “አረንጓዴ አብዮት“ ያመሩት፡፡ በ1964 አባዛኛው የእስያ ሕዝብ የሚመገበው በአዳዲስ ድቅል እጽዋት እና በአፈር አልሚ ኬሚስትሪ በመጠቀም ነበር፡፡ አሜሪካዊያን ገበሬዎች በአሁኑ ወቅት በቅጠሎቻቸው እና በግንዶቻቸው ውስጥ ፀረ-ተባዮችን በሚተፋ በቆሎን እና ድንችን በመሳሰሉ በአዳዲስ ድቅል እጽዋት ዓይነቶች ይጠቀማሉ፡፡

  2. ፬. የቴክኖሎጂ ችካሎች በምግብ እና በእርሻ ውስጥ ፬.2 የሰብል ክብካቤ እና የተባይ አወጋገድ የቦርዷ ዘዴ እና ሻገት-ገዳዮች በ1882 ፈረንሣዊው አጥኚ-እጽዋት (ቦታኒስት) ፒየር ኤም.ኤ. ሚላርዴት በፈረንሣይ የወይን እርሻ ውስጥ አጣቆን በውጤታማነት ለመውጋት በፈሳሽ በሟሟ የመዳብ ሰልፌት እና ውሃ ውስጥ በረጠበ ኖራ (የቦርዷ ድብልቅ) መጠቀም ጀመረ፡፡ ይህ የቦርዷ ድብልቅ ነው በአሁኑ ወቅት ሰብሎችን የመያጠቁትን አያሌ ሻገቶች የሚቆጣጠረው፡፡ በእዚህ ዘዴም ነበር የመጀመሪያው ፀረ-ተባይ ጥቅም ላይ የዋለው እና ኬሚካዊ የሰብል ጥበቃ ስር-ነቀል ለውጥ ያመጣው፡፡ በእርሻ ፀረ-ሻገቶች ውስጥ ኬሚካዊ ፈጠራዎች የቀጠሉት በ1934 ዲቲዮካርባሜት ፀረ-ሻገቶችን እና በ1996 ስትሮባይሉሪን ፀረ-ሻገቶችን በማቅረብ ነበር፡፡ ዲዲቲ እና ፀረ-ተባዮች ፀረ-ተባዮች የእርሻ ሰብሎች በሻገቶች፣ በነፍሳት እና ከሌሎች ተክሎች ጋር በመወዳደር እንዳይጎዱ ሽፋን ይሰጣሉ፡፡ ፖል ሚዩለር የድንች ጢንዚዛዎችን እና ተውሳኮችን ለመቆጣጠር በ1939 በዋጋ ወድ ያልሆነውን ፀረ-ተባይ፣ ዲዲቲን (dichlor-diphenyl-trichlorethan) ሠራ፡፡ ዲዲቲ እና ሌሎች ተመሳሳይ ፀረ-ተባዮች የሰበል ተባዮችን እና ነፍሳት-ወለድ በሽታዎችን ከሃያ ዓመታት ይበልጥ ሲቆጣጠሩ የቆዩ ነበሩ፡፡ በ1960ዎች ውስጥ ግን የሥነ-ምሕዳር መጎጋት እና ዲዲቲ በስውአካል ውስጥ መጠራቀሙ ሕዝብ ላይ ያሳደረው ስጋት ተዋሳኮች መድሐኒቱን በመቋቋማቸው ወደ አዳዲስ ፀረ-ተባዮች ፈጠራ ከማምራቱ ጋር ተደምሮ ዲዲቲ ተፈላጊነቱ አሽቆለቆለ፡፡ ዛሬ በተግባር ላይ የዋሉት ፀረ-ተባዮች ለገበሬዎች ከፍተኛ ምጣኔሃብታዊ ጥቅም ከመስጠታቸውም ሌላ፣ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ለሥነ-ምሕዳር ተስማሚ ናቸው፡፡ ዲዲቲ ወባን ሲወጋ በዲዲቲ መንስኤነት የሳሱ የእንቁላል ቅርፊቶች የከብቶች ክብካቤ የከብት በሽታዎችን በክትባት ወይም በሕክምና ማከም የምግብ አቅርቦትን ጥራት እና ብዛት ለመጨመር አስችሏል፡፡ ሉዊ ፓስተር ተፈጥሯዊ- የአካል-መከላከያን በማንቃት አንትራክስ-አምጪ ሕዋስን ለመከላከል በ1881 እንሰሳት የሚከተቡባቸውን ቴክኒኮች በስኬታማነት አጠራ፡፡ በ1981 ደግሞ ዓይነታቸው የተለያየ ተወሳኮችን፣ ትላትሎችን እና የእንሰሳትን ጤንነት የሚያውኩ ሌሎች ውስጣዊ ጥገኞችን የሚወጋው ፀረ-ጥገኛ-ትላትሉ፣ አይቨርሜክቲን ተቀመመ፡፡ በአሁኑ ወቅትም አመንዣጊ እንሰሳትን አስተላላፊ ወኪልን በማስጠለል በእንሰሳት መኖ ውስጥ በሚገኝ ፕሮቲን መንስኤነት የሚከሰተውን “የእብድ ላም በሽታ“ ተብዬውን ከስፖንጂፎርም ኤንሴፋሎፓቲ (BSE) የሚከላከል መድሐኒት ለመቀመም ምርምራዊ ሙከራ እየተከናወነ ነው፡፡ ሉዊ ፓስተር የእርሻ ሜካናይዜሽን ለእርሻ ኬሚካሎች (ማዳበሪያዎች፣ ፀረ-ተባዮች፣ ወዘተ.) ብሎም ለውሃ፣ ለእርሻ ኬሚስትሪ እና ለእርሻ ሜካናይዜሽን ውጤታማነት የሚያስፈልጉ ተግባራዊ ቴክኖሎጂዎች በሥራ ላይ የዋሉት ባለፈው ምእት-ዓመት ውስጥ ነበር፡፡ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች የግብርናን ውጤታማነት እና ምርታማነትን በእጅጉ ያሳደጉ ናቸው፡፡ በለ ናፍጣ-ዘይት-ኃይሉ ትራክተር በአሜሪካዊው ፈልሳፊ በቤንጃሚን ሆልት በ1904 ተሠራ፡፡ የዛሬዎቹ ትራክተሮች፣ ማጨጃዎች፣ ኮምባይኖች፣ ፈልፋዮች፣ የመስኖ ማሺኖች፣ መሠረተ-ኮምፒዩተር ተተግባሪ ቴክኖሎጂ እና የረቀቀው GPS ሁሉ የጎለበቱት ፔትሮክሚካዊ ነዳጆችን፣ መዋቅራዊ ቁሶችን (የብረታ-ብረት ቅለቅሎችን እና ምጡቅ ፕላስቲኮችን)፣ የጎማ ቴክኖሎጂን እና አስሊ ኤሌክትሮኒኮችን በመሳሰሉ ኬሚካዊ ፈጠራዎች ነው፡፡ አመናዊ ኮምባይን-ሃርቨስተር ሆልት የፈለሰፈው ተንፏቃቂ ትራክተር

  3. ፬. የቴክኖሎጂ ችካሎች በምግብ እና በእርሻ ውስጥ ፬.3 የምግብ አቀነባበር፣ አያያዝ እና ደኅንነት ሳካሪን እና አጣፋጮች በኬሚስትሪ በመጠቀም የተፈጠሩት ሰው-ሠራሽ አጣፋጮች የስኳር ወሰዳን በመቆጣጠር ረገድ የስኳር-ሕሙማንን እና የመጠነ-አካል-ጠባቂዎችን (dieters) የረዳሉ፡፡ ሰው-ሠራሹን አጣፋጭ፣ ሳካሪንን በ1901 ያመረተው ጆን ኤፍ. ኴኒ ነበር፡፡ በ1967 ደግሞ የበቆሎን ወለላ በፍራፍሬ/ማር-ንጥር-ስኳር (fructose) ጣፋጭነት ከ14% ወደ 42% ለማሳደግ በተፈቀደ ኤንዛይም በመጠቀም ከፍራፍሬ/ማር-ንጥር-ስኳር የበቆሎ ወለላ (syrup) መረብረክ ተጀመረ እና ወዲያውኑ ለሁሉማ ዓበይት ለስላሳ መጠጦች አጣፋጭ ሆነ፡፡ አስፓርታሜ አሜሪካ ውስጥ በመጀመሪያ የተሸጠው በ1985 ነበር፡፡ ኑትራስዊት በሚል ስያሜ ለገበያ የቀረበው ይህ ባለ ዝቅተኛ-ካሎሪ በጣም አጣፋጭ በ1955 የተቀመመው ለፀረ-አልሰር መድሐኒትነት ነበር፡፡ ተዳማሪ ቪታሚኖች የምግብ ባዮኬሚስትሪ እውቀት ለተመጣጠነ-ምግብ ጉድለቶች እና በቪታሚኖች አለመኖር ሳቢያ መንስኤነት ለሚከሰተው የተመጣጠነ-ምግብ-እጥረት ፈውሶችን በማቅረብ ስር-ነቀል ለውጥ አመጣ፡፡ በመጀመሪያ የተገኘውን ቪታሚን በመመርመር እንደታየው፣ በእዚህ መስክ ውስጥ ታላላቅ ግስጋሴዎችን ያደረገው ኬሚስትሪ ነበር፡፡ ለእይታ እና ለኤፒቴሊያ መከላከያ መሠረታዊ ንጥረ-ምግብ የሆነው ቫይታሚን ኤ (ቤታ-ካቶቴኒ) በ1913 የተቀመመው ከቅቤ እና ከእንቁላል አስኳሎች ነበር፡፡ ኬሚካዊ መዋቅሩ የታወቀው በ1931 ሲሆን፣ በመጀመሪያ የተቀመመው ደግሞ በ1947 ነበር፡፡ ሁንጋሪያዊው ባዮኬሚስት አልበርት ዜንት-ጊዮርጊ አሁን ቪታሚን ሲ ተብሎ የሚታወቀውን ሄክሱሮኒክ (አስኮርቢክ)አሲድን በ1928 ከኩላሊት (adrenal) እጢዎች ነጥሎ አወጣ፡፡ ዓይነ-ስውርነትን እና ሌሎች የንጥረ-ነገር-እጥረት በሽታዎችን ለመውጋት ፕሮ-ቪታሚን ኤ የሚመረትበት ዘረ-መላዊ-ልውጡ “ወርቃማው ሩዝ“ በ2001 እስያ ውስጥ ገባ፡፡ የማቆያ እና የፍብረካ ግስጋሴዎች በ19ኛው ምእት-ዓመት አጋማሽ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የስጋ ንጥርን በሠራው ጀርመናዊው ዩስቱስ ላይቢግ አማካኝነት የምግብ ኬሚስትሪን አጀማመር እናስታውሳለን፡፡ በማቆያ እና በፍብረካ ቴክኒኮች ውስጥ የተደረጉት ግስጋሴዎች ምስጋና ይግባቸው‘ና የተቀነባበሩ ምግቦችን ለማዘጋጀት እንችላለን፡፡ የምግብ ኬሚስትሪ ኢንዱስትሪያዊ ትግበራዎችን በማሳለጡ ምክንያት ነበር በርካታ አዳዲስ የተቀነባበሩ ምግቦችን ለማምረት የተቻለው፡፡ አዳዲስ ቴክኒኮች አቀዝቅዞ-ማድረቅን (liophilisation) [1939] እና ከፍራ-ፍሬ ፈሳሾች ድፍድፎች (concentrates) [1946] መሥራትን አካትቶ ምግብን የማከማቸት ዕድሜ ጭምር ያራዝማሉ፡፡ የላይቢግ ስጋ ንጥር የድሮ ማስታወቂያ የምግብ ደኅንነት እና ጥራት ቁጥጥር ማንኛቸውም ጥሬ የእርሻ ምርት ወይም የተዘጋጀ ምግብ ሊበከል እና የሰውን ጤንነት ሊያውክ ይችላል፡፡ ብከላ የሚከሰተው በዝግጅት፣ በማብሰል፣ በማቅረብ ወይም በማከማቸት ወቅት ነው፡፡ የምግብን ደኅንነት ከሚጨምሩት ኬሚካዊ ግስጋሴዎች መካከል ማይክሮባዊ የምግብ በካዮችን ለማወቅ የሚያስችሉ ፈጣን የጥራት ቁጥጥር ዘዴዎች፣ ብሎም ከ1997 አስከ 1999 ድረስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 20% የምግብ-ወለድ ወረርሽኞችን እና ከምግብ-ወለድ በሽታ-አምጪዎች (pathogens) የሚጋቡ በሽታዎችን ያስቀነሱት ቁጥጥሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

  4. ፬. የቴክኖሎጂ ችካሎች በምግብ እና በእርሻ ውስጥ ፬.4 የምግብ አከመቻቸት የምግብ አሰተሻሸግ ምግብን በፕላስቲኮች፣ በብረቶች፣ በመስተዋት እና በሴራሚክ ቴክኖሎጂዎች ማሸግ በሽያጭ፣ በአላላክ እና በዝግጅት ወቅት ምግብን ለማቆየት ይረዳል፡፡ ራልፍ ዊሌይ ኢንዱስትሪያዊ ሳራን ፖሊመር የሚባለውን ፕላስቲክ በ1930ዎች ውስጥ ፈለሰፈ እና ኦክሲጂንን፣ እርጥበትን፣ ሽታን፣ ብሎም በከረረ ወበቅ እና መጠነ-ሙቀት ጊዜ ኬሚካሎችን የሚከላከለው ሳራን መጠቅለያ በ1953 ለገበያ ወጣ፡፡ ሳራን መጠቅለያ የቫይኒሊዲን ክሎራይድ እና የቫይኒል ክሎራይድ ረጋ-ሠራሽ ፕላስቲክ (copolymer) ነው፡፡ ከሌሎች ፈጠራዎች መካከል ደግሞ አሉሚኒየም ጣሳዎችን ለምግቦች እና ለመጠጦች ማሸጊያነት (1960ዎች)፣ ብሎም መስታወትን ወይም አሉሚኒየምን ለመተካት PETን (polyethylene terephthalate)ን ለታዳሽ ኮንቴይነር ማሸጊያነት (1970ዎች) ጥቅም ላይ በመዋላቸው ተጠቃሽ ይሆናሉ፡፡ አቀዝቃዦች እና ክሎሮፍሎሮካርቦኖች ማቀዝቀዣ በ1918 ለቤት ጥቅም መዋል ከጀመረ ወዲህ ትኩስ ምግቦችን በደኅንነት በማጓጓዝ እና በማከማቸት ረገድ የምግብ አቆያየትን ለውጧል፡፡ ማቀዝቀዣዎች በ1920ዎች መባቻ ውስጥ አቀዝቃዡ ድኚ (sulfur) ዳይኦክሳይድ መርዛማ መሆኑ ከተደረሰበት በኋላ ተፈላጊነት አጡ፡፡ መፍትሄው ቶማስ ሚድግሌይ እና ቻርለስ ኬተሪንግ በ1931 ወደ አቀዝቃዥ ጋሰነት የለወጡት ከክሎሮፍሉሮካርቦን አንዱ የሆነው የፍሪኦን 12 ውህድ (CFS, CCI2F2 ተብሎም ይጠራል) ሆነ፡፡ በእዚህን ጊዜ ነበር ማቀዝቀዣዎች በፍጥነት በመኖሪያ-ቤቶች፣ በምግብ-ቤቶች እና በመደብሮች ውስጥ መደበኛ መገልገያዎች የሆኑት፡፡ አሁን ግን የምድርን ኦዞን ልባስ በማውደሙ ምክንያት የፍሪኦን ሚና እየተቋረጠ ነው፡፡ የበረዶ-ሣጥን (1890) እና ዘመናዊ ማቀዝቀዣ ማይክሮዌቭ ምድጃዎች የ20ኛው ምእት-ዓመት የቤት ውስጥ መገልገያ መሣሪያዎች የእለት-ከእለት የምግብ ዝግጅትን አድካሚነት በእጅጉ ያስወገዱ ናቸው፡፡ በኬሚካዊ ግስጋሴዎች አሳላጭነት እውን ከሆኑት ከእነዚህ የቤት ውስጥ መገልገያ መሣሪያዎች መካከል አንዱ ማይክሮዌቭ ምድጃ ነው፡፡ ፔርሲ ኤል. ስፔንሰር በ1945 ሬይተን ከተማ ውስጥ ከአንድ የራዳር ማስተላለፊያ አጠገብ ቆሞ ሳለ በኪሱ ውስጥ የያዘው የከረሜላ አሞሌ መሟሟት ጀመረ፡፡ በእዚህ የተደነቀው ስፔንሰር ይህንኑ አሠራር በፈንዲሻ ላይ ሞከረ እና ማይክሮዌቭ ምድጃ እውን ለመሆን በቃ፡፡ ‹ራዳሬንጅ› በሚል ስያሜ በእርሱ የተሠራው ማይክሮዌቭ ምድጃ በእዚያ አሥርተ-ዓመት ወደነበሩት ኢንዱስትሪያዊ ማእድ-ቤቶች ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል ጀመረ፡፡ ዛሬም ማግኔትሮን የሚባሉት የ፪ኛው የዓለም ጦርነት ዓይነት ትራንስሚተሮች የእዚህ ተወዳጅ መገልገያ መሣሪያ የደም-ስር ናቸው፡፡ የሃይፖክሎረስ አሲድ ሞሊኪዩል ንጹሕ ውሃ በኬሚስትሪ ውስጥ የተደረጉ ግስጋሴዎች ከባክቴሪያዎች፣ ከቫይረሶች እና ከሌሎች ጎጂ በካዮች ነጻ የሆነ አስተማማኝ ውሃ ለመቅረቡ ማረጋገጫ ናቸው፡፡ በእዚህ መስክ ውስጥ ከተከናወኑ ፈጠራዎች መካከል መጥፎ ጣእምን እና ሽታን ለማስወገድ በካርቦኖች፣ ውሃን ለማለስለስ እና ከባድ ብረቶችን ለማስወገድ በሌሎች ንጥረ-ነገሮች፣ ብሎም ውሃን ለማከም፣ ለማቅረብ እና ለማከፋፈል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጠቀም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በውሃ ማከሚያ ሥርዓቶች ውስጥ የክሎሪን መድሐኒትነት የተጀመረው በ1910 ሲሆን፣ የቤት ውስጥ አንጪ የተዋወቀወ ደግሞ በ1913 ነበር፡፡ መሠረተ-ክሎሪን ተባይ-ገዳዮች ማእድ-ቤቶችን እና የምግብ ማቀነባበሪያዎችን ከምግብ-ወለድ በሽታዎች ለመከላከል ዛሬም ግሩም ዘዴዎች ናቸው፡፡

More Related